በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነዳጅ ጭቅጭቅ የአሜሪካና የሳውዲን የቆየ ሽርክና እየጎዳ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ እና የሳውዲ አረቢያ ባንዲራዎች ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጉብኝት በፊት፣ ጅዳ፣ ሳውዲ አረቢያ 7//14/2022
የዩናይትድ ስቴትስ እና የሳውዲ አረቢያ ባንዲራዎች ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጉብኝት በፊት፣ ጅዳ፣ ሳውዲ አረቢያ 7//14/2022

በሳውዲ አረቢያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በነዳጅ ምክንያት የተነሳው ንትርክ በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረውን የቆየ ወዳጅነት እያሻከረው ነው ተብሏል።

የሳውዲ ባለሥልጣናት ከነዳጅ ላኪ ሀገሮች ድርጅት ወይም በእንግሊዝኛው ምጻረ-ቃል “ኦፔክ” ጋር በመሆን የነዳጅ ምርትን በቀን በ2 ቢሊዮን በርሜል ለመቀነስ በቅርቡ ተስማምተዋል።

ሳውዲዎቹ እንደሚሉት ውሳኔው ያስፈለገው የነዳጅ ዋጋን ከማሽቆልቆል ለመግታት ነው። የጉዳዩ ባለሙያዎች እንደሚሉት ደግሞ፣ ውሳኔው በሩሲያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ የሚያዳክም ሲሆን፣ የሃይል ዋስትናንም ይጎዳል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከወራት በፊት በሳውዲ ጉብኝት አድርገው ከአልጋ ወራሽና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን ሳልማን ጋር መገናኘታቸውና የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ ተጨማሪ እንዲመረት ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱን በተመለከተ የዜና አውታሮች በሰፊው እየዘገቡት ይገኛሉ።

ተንታኖች እንደሚሉት አልጋ ወራሹ ለፕሬዚዳንት ባይደን የገቡትን ቃል በልተዋል። እስከ ዓመቱ መጨረሻ የነዳጅ ምርትን በቀን በ750 ሺህ በርሜል ለመጨመር ቃል ገብተው ነበር።

XS
SM
MD
LG