“የመዋዕለ ንዋይ ፍሰቱ እንዳይቋረጥ” ሲሉ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት አሳስበውኛል። ያ ማለት ግን፤ ጉዳዩን በሚመለከት ምንም አያደርጉም ማለት አይደለም። ለወንጀሉ ተጠያቂ የሚያደርግ .. ምንም ይሁን ምን .. የሆነ ቅጣት መኖር አለበት።
አንዳንዶች ደግሞ የሚመጣውን የመዋዕለ ንዋይ .. የአራት መቶ ሃምሳ ቢልዮን ዶላር የማይፈልጉ መሆናቸውን ነግረውኛል። ያ ያላዋቂ ሃሳብ ይመስለኛል።
ይሁን እንጅ እንደዚያ የሚያስቡም አሉ። ስለሆነም፤ በመጨረሻው መውሰድ ያለብንን እርምጃ አስመልክቶ በትብብር አብረውኝ እንዲሠሩ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ነው የምተወው።” ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ።
ዩናይትድ ስቴትስ ኢስታንቡል ከሚገኘው የሪያድ ኤምባሲ ውስጥ በተገደለው የሳውዲው ጋዜጠኛ የጅማል ካሾግጂ ጉዳይ “እጃቸው አለበት” ያለቻቸውን 21 ሰዎችን የቪዛ ፍቃድ ሰረዘች።
ግድያውን አስመልክቶ የተለያዩ ሃሳቦች የሰነዘሩት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው ለሳውዲ አረብያ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ ለመሸጥ ቀደም ሲል ያደረጉትን ስምምነት በተናጠል ከመሰረዝ ይልቅ ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ጋር በቅርበት መሥራት የሚመርጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ለተጨማሪ መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ