በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊያቀኑ ነው


የዋይት ሓውስ ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቨን
የዋይት ሓውስ ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቨን

የዋይት ሓውስ ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቨን፣ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቅንተው፣ አገሪቱ ከእስራኤል ጋራ ያላትን ግንኙነት ስለምታሻሻልበት መንገድ ከሪያድ መሪዎች እንደሚመክሩ ታውቋል።

ሰለቨን ጉዞ እንደሚያደርጉ ያስታወቁት፣ “የቅርብ ምሥራቅ ፖሊሲ” የተሰኘው ተቋም፣ በትላንትናው ዕለት በአዘጋጀ አንድ ሲምፖዚየም ላይ ነው።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የሕንድ ተወካዮችም፣ ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመጓዝ፣ በኒው ደልሂ እና በባሕረ ሠላጤው አገሮች መካከል፣ እንዲሁም በአሜሪካ እና በተቀረው የቀጣናው አገሮች መካከል ስለሚኖር ዐዲስ ትብብር እንደሚመክሩ፣ ሰለቨን በተጨማሪ አስታውቀዋል።

ሰለቨን በሪያድ፣ ከሕንድ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቻዎቻቸው ጋራ እንደሚገናኙ ይጠበቃል።

በእስራኤል እና በሳዑዲ መካከል ያለውን ግንኙት ለማሻሻል ፍላጎት አለን። የመጀመሪያው ተጨባጭ ውጤት የታየውም፣ በባይደን አስተዳደር ጥረት ነው። ይህም በሳዑዲ የአየር ክልል ላይ፣ የእስራኤል የመንገደኞች አውሮፕላን እንዲበር አስችሏል፤”

“በእስራኤል እና በሳዑዲ መካከል ያለውን ግንኙት ለማሻሻል ፍላጎት አለን። የመጀመሪያው ተጨባጭ ውጤት የታየውም፣ በባይደን አስተዳደር ጥረት ነው። ይህም በሳዑዲ የአየር ክልል ላይ፣ የእስራኤል የመንገደኞች አውሮፕላን እንዲበር አስችሏል፤” ብለዋል ሰለቨን።

“በመጨረሻም ግባችን፥ ግንኙነቱን ሙሉ ለሙሉ ማሻሻል ነው፡፡ ይህም፣ የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ፍላጎት ነው፤” ሲሉ አክለዋል።

ከእስራኤል በቀጥታ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሐጅ የመንገደኞች በረራ እንደሚጀምር፣ የባይደን አስተዳደር ባለፈው ዓመት አስታውቆ ነበር።

በእስራኤል እና በፍልስጥኤም የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ የመካ ጉዟቸውን የሚያደርጉት በሦስተኛ ሀገራት በኩል ነው።

ካለፈው ሦስት ዓመት ወዲህ፣ የእስራኤል አየር መንገዶች፥ የሳዑዲ አረቢያን የአየር ክልል አልፈው ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ባሕሬን እንዲበሩ ሪያድ ፈቅዳለች።

XS
SM
MD
LG