በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በደቡብ አፍሪካ ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጣለች


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት

ዩናይትድ ስቴትስ ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ ለሚጠራው ቡድን የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ይሰጣሉ ባለቻቸው አፍሪካ ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ ማዕቀቦችን ደንግጋለች።

ዩናይትድ ስቴትስ ይህንን ዕርምጃ ስትወስድ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለተኛዋ ነው። ሁለተኛው ዙር ማዕቀብ ያነጣጠረው "በዩናይትድ ስቴትስ ጥቅሞች ላይ ጥቃት ለማድረስ ፍላጎት ያለው እና እያቀደም የሚገኝ" ተብሎ የተወነጀለ "ፋርሃድ ሁመር" የተባለ ግለሰብ ጨምር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባሉ አካላት ላይ መሆኑን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ሳምንት "የሶማሊያ እስላማዊ መንግሥት የጦር መሣሪያ አስተላላፊ ህዋስ" ስትል በጠራችው ቡድን ላይ ማዕቀብ መደንገጓን የገንዘብ ሚኒስቴሯ አስታውቋል።

እስላማዊ መንግሥት ቡድን ኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ ከገጠመው ሽንፈት በኋላ አፍሪካ ውስጥ እንቅስቃሲውን እያስፋፋ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሪፖርቶች አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG