በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ከሩሲያ ጋር መደራደር የማይቻል ነው” ዜሌንስኪ


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ

ሩሲያ አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደ ራሷ ከጠቀለለች በኋላ፣ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ጋር መደራደር “የማይቻል” መሆኑን ለማስረገጥ ዛሬ ማክሰኞ የወጣ ዐዋጅ ላይ ፈርመዋል።

“ሩሲያ ዜሌንስኪ ሃሳባቸውን እስኪቀይሩ ወይም በዩክሬን አዲስ ፕሬዚዳንት እስከሚመጣ ትጥብቃለች” ብለዋል የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለዜና ሰዎች።

የሩሲያ የላይኛው ፓርላማ አራቱ ይዩክሬን ግዛቶች ወደ ሩሲያ መጠቃለላቸውን ዛሬ አጽድቋል። ድርጊቱ በዩክሬንና በምዕራብ አጋሮቿ ሲወገዝ፣ የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ፣ ድርጊቱን “አደገኛ ማባባስ” ካሉ በኋላ፤ “ምንም ህጋዊ ዋጋ” የሌለው ሲሉ ገልጽውታል።

የሩሲያ የታችኛው ፓርላማ (ዱማ)፣ ቀደም ብሎ ነበር የዩክሬን ግዛቶች ወደ ሩሲያ መጠቃለላቸውን ያጸደቀው።

“በአራቱ ግዛቶች የተካሄደው ድምፀ ውሳኔ፣ በአስገዳጅ ሁኔታ የተካሄድና የነዋሪዎቹን ፍላጎት የማይወክል ነው” ብላለች ዩክሬን።

“በማስፈራራትና በኃይል የሌላን ሀገር ግዛት መቀላቀል የተመድ ቻርተርንና ዓለም አቀፍ ህግጋትን የሚጻረር ነው” ሲሉ ጉቴሬዥ ባለፈው ሳምንት ተናግረዋል።

ሩሲያ ግዛት ነጠቃ ላይ ባለችበት በዚህ ወቅት፣ የዩክሬን ኃይሎች በመልሶ ማጥቃት ድል እያገኙ እንደሆነ ይነገራል።

ዜሌንስኪ በምሽት የቪዲዮ መልዕክታቸው ሰራዊታችው ወደፊት እየገሰገሰ እንደሆነና በርካታ ከተሞችን መልሶ መቆጣጥሩን ገልጿል።

አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን እንዳሉት ደግሞ፣ “የሩሲያ ኃይሎች ወደ ምዕራብ አቅጣጫ እየገፉ ባለበት ወቅት፣ ውጊያው ቀጣይ እንደሚሆን እንገምታለን፤ ነገር ግን፣ የዩክሬን ኃይሎች ይዞታቸውን እየተከላከሉ በመሆኑ፣ ምንም እርምጃ አያሳይም።”

XS
SM
MD
LG