በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረትና ዩክሬን የወታደራዊ ርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ እና የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል በብራስልስ የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እአአ ሰኔ 27/2024
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ እና የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል በብራስልስ የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እአአ ሰኔ 27/2024

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ትላንት ብራስልስ በተካሄደው የአውሮፓ ኅብረት ስብሰባ ላይ በመገኘት ከኅብረቱ ጋራ ለተፈረመው የረዥም ጊዜ የፀጥታ ስምምነት አባል ሃገራቱን አመስግነው፣ ቃል የተገባው ወታደራዊ ርዳታም በአስቸኳይ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል እና የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሰላ ቮን ደር ላየን ከዜለኒስኪ ጋራ በመሆን ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

ዩክሬን ሦስት ዓይነት የፀጥታ ስምምነት ተፈራርማለች። የመጀመሪያው በአጠቃላይ ከአውሮፓ ኅብረት ጋራ ሲሆን፣ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ከሊትዌኒያ እና ኢስቶኒያ ጋራ መሆኑ ታውቋል።

ዜለንስኪ ወደ ስብሰባው ከማቅናታቸው በፊት በ X ማኅበራዊ ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት መልዕክት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉንም የኅብረቱ 27 ሃገራት ያካተተ ስምምነት መሆኑን እና በተቋሙ ውስጥ ለውጥ ቢኖር እንኳ፣ ዩክሬን ቀጣይ እገዛ የምታገኝበት ሁኔታን እንደፈጠረ አስታውቀዋል። በሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ተጨማሪ ጫና መፍጠር እንደሚያስፈልግም በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG