በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ኢላማ ባደረጉ የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ በማካሄድ ልትወነጅል ተዘጋጅታለች


የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ

የባይደን አስተዳደር ሩሲያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ባነጣጠሩ የሃሰት መረጃ ቅስቀሳዎች ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆኑን ስለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ሰዎች ተናገሩ፡፡

ከመግለጫው በፊት በይፋ መናገር ያልተፈቀደላቸው በመሆኑ ስማቸው ያልተገለጸ ሰዎችን ጠቅሶ አሶሴይትድ ፕሬስ እንደዘገበው የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ ዛሬ ረቡዕ ስለጉዳዩ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የስለላ ተቋማት ቀደም ሲል ሩሲያ በምርጫው ውስጥ ጣልቃ ለመግባት በመሞከር የተሳሳተ መረጃ ተጠቅማለች በማለት ክስ ሰንዝረዋል።

በጠቅላይ አቃቢ ህጉ ጋርላንድ ይፋ የሚደረገው ክስ የዩናይትድ ስቴትስ ስጋቶችን ጥልቀት እና በተጠርጣሪዎች ተሳታፊዎች ላይየሚወሰዱ ህጋዊ ርምጃዎችን ከወዲሁ እንደሚያሳይ ይጠበቃል።

ስለ ጉዳዩ በፍትህ ሚኒስቴር የምርጫ ስጋት ግብረ ሃይል ስብሰባ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን ከስብሰባው መግቢያ በፊት ጋርላንድ እና ሌሎች የህግ አስፈጻሚው መሪዎች ስለጉዳዩ አጭር ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቅሷል፡፡

መግለጫው ከሚያካትታቸው መካከል የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ስለሚያሰራጩት የሀሰት መረጃዎችና ፕሮጋንዳዎችን እንደሚጨምር ዘገባው አመልክቷል፡፡

ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሊሳ ሞናኮ ሩሲያ ለምርጫው ዋነኛ ስጋት መሆኗን ባላፈው ወር ተናግረዋል፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ስለጉዳዩ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG