የሩሲያ የመከላከያ ሚንስቴር የአየር ጥቃት መከላከያ ኅይሎቻችን የዩክሬይንን 22 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥለዋል ሲል ተናገረ፡፡
አስራ አምስቱን ብሪያንስክ ፍለ ግዛት ስድስቱን ደግሞ በሩስያ ቁጥጥር ስር ባለችው ክራይሚያ እንዲሁም አንዱን ድሮን ሊፕትሴክ ውስጥ መጣሉን ነው ሚንስቴሩ ያስታወቀው፡፡
ኩርስክ በተባለው የዩክሬይን አዋሳኝ ግዛትም ሶስት ድሮኖች ተመትተው ወድቀዋል ሲሉ የክፍለ ግዛቷ አገረ ገዢ ተናግረዋል፡፡
የዩክሬይን የጦር ኅይል በበኩሉ ሩሲያ በበርካታ አካባቢዎች የአየር ጥቃት ታደርሳለች ሲል ዛሬ ማስጠንቀቁም ተመልክቷል፡፡ የድኒፕሮፐትሮቭስክ አገረ ገዢ በሰጡት ቃል ሩሲያ በድሮን እና በመድፍ ባደረሰችው ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ቤቶች እንደወደሙ ገልጸዋል፡፡ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ግን እንደሌለ አስታውቀዋል፡፡
መድረክ / ፎረም