በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜሌንስኪ በሩስያ በመደብደብ ላይ ያለችውን የኻርኪቭ ከተማ ጎበኙ


የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ሩስያ ድብደባ በምታካሂድበት የዩክሬይን ሰሜን ምስራቃዊ ክፍለ ግዛት የምትገኘውን ኻርኪቭ ከተማን ዛሬ ሐሙስ ጎበኙ
የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ሩስያ ድብደባ በምታካሂድበት የዩክሬይን ሰሜን ምስራቃዊ ክፍለ ግዛት የምትገኘውን ኻርኪቭ ከተማን ዛሬ ሐሙስ ጎበኙ

የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ሩስያ ድብደባ በምታካሂድበት የዩክሬይን ሰሜን ምስራቃዊ ክፍለ ግዛት የምትገኘውን ኻርኪቭ ከተማን ዛሬ ሐሙስ እንደጎበኙ ገለጹ፡፡ የተጓዙት በክፍለ ግዛቱ ያሉትን ወታደራዊ ባለስልጣናት ለማነጋገር መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ዜሌንስኪ በማሕበራዊ መገናኛቸው “የኻርኪቭ ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪ ነው ሆኖም በአጠቃላዩ ሁኔታውን እየተቆጣጠርነው ነው” ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡

ባለፉት ቀናት ሩስያ ኻርኪቭ ውስጥ በርካታ መንደሮችን መያዟን የገለፀች ሲሆን፣ የሩስያ ኃይሎች እየገፉ መሆናቸው ዜሌንስኪ በዕቅድ የያዟቸውን በርከት ያሉ የውጪ ሀገር ጉብኝቶች እንዲሰርዙ አስገድዷቸዋል፡፡

የዩክሬይን የጦር ኃይል ዛሬ ሐሙስ ባወጣው መግለጫ፣ የኻርኪቭ ሁኔታ አሁንም የተወሳሰበ መሆኑን አመልክቶ፣ ሆኖም ኃይሎቹ እያረጋጉት መሆኑን እና በአንዳንዶቹ አካባቢዎች በማጥቃት ያሉትን የሩስያ ኃይሎች እየመከቱ መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ከሁለት ቀናት በፊት ዩክሬይንን የጎበኙ ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ኻርኪቭን ለመከላከል የሚያስችል የአየር ጥቃት መከላከያ እንድትለግስ ፕሬዚደንት ዜሌንስኪ ጠይቀዋቸዋል፡፡ ብሊንከንም ባለፈው ወር ከተፈቀደው የ61 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ጥቅል አካል የሆነ የ2 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ይፋ አድርገዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG