በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩስያ የቦምብ ጥቃት ሙከራ ማክሸፏን አስታወቀች


ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ ፌደራል ደህንነት አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ሞስኮ፣ ሩስያ እአአ ኅዳር 16/2018
ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ ፌደራል ደህንነት አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ሞስኮ፣ ሩስያ እአአ ኅዳር 16/2018

በሰሜናዊ ሩስያ በመንግሥት አስተዳደር ህንጻ ላይ የቦምብ ጥቃት ለማድረስ ያቀደ ያላችውን ቤላሩሳዊን መግደሏን ሩሲያ አስታወቀች።

ግለሰቡ ጥቃቱን ሊያደርስ ያቀደው ዩክሬንን ወክሎ ነበር ሲል የሩስያ ፈዴራል ጸጥታ አገልግሎት ገልጿል።

ቤላሩሳዊው ቤት ውስጥ በተዘጋጀ ፈንጂ ጥቃቱን ለማድረስ ያቀደው ሩስያን ከፊንላንድ ጋራ በሚያዋስነው ድንበር 250 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው “ኦሎኔት” የተባለች ከተማ ውስጥ እንደነበረ ተገልጿል። ከዩክሬን በኩል እስካሁን የተሰጠ አስተያየት የለም።

በሌላ በኩል በደቡባዊ ዩክሬን ከተማ ከባድ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱ ተዘግቧል፡፡ ፍንዳታው የተሰማው የዩክሬን ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ እና የግሪክ ጠቅላይ ሚንስትር ኪሪያኮስ ሚትሶታኪስ በጦርነት በዳሸቀው አካባቢ ጉብኝታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ሳሉ ነው። “መኪናችን ውስጥ እየገባን ሳለን የፍንዳታ ድምጽ ሰምተናል” ያሉት የግሪኩ ጠቅላይ ሚንስትር ፍንዳታው ፣“ኦዴሳ አሁንም በጦርነቱ እንደተጠመደች መሆኗን አስታውሶናል” ብለዋል። በፍንዳታው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች እንደተገደሉ ዜሌንስኪ ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ኡርሱላ ቮን ደ ሊየን በግሪኩ መሪ ጉብኝት ወቅት የተፈጸመውን ጥቃት “ ሌላ የሽብርተኝነት ሙከራ” በማለት አውግዘዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG