በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ሚሳዬሎች ኪቭና ሚኮላይቭን አጠቁ


የዩክሬን ፕሬዚዳናት ቮሎድሚር ዜለነስኪ
የዩክሬን ፕሬዚዳናት ቮሎድሚር ዜለነስኪ

የዩክሬን ፕሬዚዳናት ቮሎድሚር ዜለነስኪ በኪቭና ሚኮላይቭ ውስጥ ዛሬ ረቡዕ በደረሱ የሩሲያ ሚሳዬል ጥቃቶች ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ተናገሩ፡፡

“አገራችን ላይ የደረሰ ሌላ ግዙፍ የሩሲያ የአየር ጥቃት” ሲሉ በማህበራዊ የመገናኛ መድረክ ላይ የተናገሩት ዜለነስኪ “ “ስድስት ግዛቶች በጠላት ጥቃት ስር ሆነዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁሉም ሠራተኞቻችን ይህ ሽብር የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ለማስወገድ እየሠሩ ነው” ብለዋል፡፡

የዩክሬን ጦር 20 ድሮኖች፣ 36 ክሩዝ ሚሳዬሎች፣ አምስት ተመሪ S-300 ሚሳዬሎች እና ሶስት የባለስቲክ ሚሳዬሎች የተካተቱበት ትልቅ የሩሲያ ጥቃቶች መዥጎድጉዳቸውን ዘርዝረዋል፡፡

የየክሬን አየር መከላከያ ከ20 ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮኖች) መካከል 15 ቱን ,፣ ከ44 ሚሳዬሎች ደግሞ 22ቱን ማምከኑን የዩክሬን አየር ኃይል አስታውቋል፡፡

ሩሲያ በማይኮሌቭ ባደረሰችው ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል በከተማዪቱ የሚገኙ በርካታ ቤቶች መውደማቸውን ዜለነስኪ ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ ህገ ወጥ ወረራዋን ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ይህ ፣ ጀግኖቹ ዩክሬናውያን በየእለቱ የሚጋፈጡት እውነታ ነው”

የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊስችኮ አንድ ባለብዙ ፎቆች ህንጻ በደረሰበት ምት በመቃጠሉ ቢያንስ 5 ሰዎች ሲሞቱ ከ30 በላይ የሚደርሱ ሌሎች ሰዎች መቆሰላቸውን ቴሌግራም ላይ ባወጡት መልእክታቸው አስታውቀዋል፡፡

ኪቭን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴቭ ቦሬል የዛሬውን ረቡዕ የዩክሬን ጉብኝታቸውን የአየር ጥቃት አደጋ ማስጠንቀቂያ ደወል እየተሰማ ከአደጋው በተጠለሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው የጀመሩት መሆኑን በኤክስ የማህበራዊ መድረክ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡

ቦሬል “ሩሲያ ህገ ወጥ ወረራዋን ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ይህ ፣ ጀግኖቹ ዩክሬናውያን በየእለቱ የሚጋፈጡት እውነታ ነው” ብለዋል፡

ዜሌነስኪ በየእለቱ ምሽቱን በሚያስተላለፉ መልዕክታቸው በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ላይ ትኩረት ያደረገ ልዩ የጦር ቅርንጫፍ መቋቋሙን አስታውቀዋል፡፡

ድሮኖቹ “ውጤታማነታቸውን በመሬት፣ በሰማይ እና በባህር ጦርነቶች ውስጥ አሳይተዋል፡፡” ሲሉ አክለዋል ዜለነስኪ፡፡

የሩሲያን የምድር ጦርነቶች እና ትልቅ መጠን ያለው ውድመት ለማስቆም የሩሲያ ኃይሎች እና መሣሪያዎቻቸው፣ የድሮን መርሃ ግብሩ ዋነኛ ትኩረት ይሆናሉ ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG