በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን አገራቸው ለዩክሬን የምትሰጠው 'ጠንካራ ድጋፍ' እንደሚቀጥል ቃል ገቡ


የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፤ ዳቮስ፣ ስዊዘርላንድ
የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፤ ዳቮስ፣ ስዊዘርላንድ

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን አገራቸው ለዩክሬን ጠንካራ እና ዘላቂ ድጋፍ መስጠቷን እንደምትቀጥል ገልጸው፣ የባይደን አስተዳደር ለዩክሬን ኃይሎች የሚሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ ለመቀጠል ያለውን ቁርጠኝነት ለዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ አረጋግጠዋል።

ብሊንከን ይህን አስተያየታቸውን ያሰሙት ዛሬ ማክሰኞ በዳቮስ ስዊዘርላንድ በመካሄድ ላይ ከሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ትይዩ ከዘለንስኪ ጋር በተነጋገሩበት ወቅት ነው። አገራቸው ለዩክሬይን ያላትን ድጋፍ የገለጸችው ኪየቭ ሩስያ በመሰረተ ልማት አውታሮቿ እና በሰላማዊ ዜጎቿ ላይ እያደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃት እየተጋፈጠች ባለችበት ወቅት መሆኑንም የዩናይትድ ስቴትሱ ከፍተኛ ዲፕሎማት አክለው አመልክተዋል። "እናም በየቀኑ እያየን ነው። ይሁን እንጂ የዩክሬንን ሕዝብ አስደናቂ ቆራጥነት እና የመቋቋም ችሎታ፤ እንዲሁም የፀጥታ ኃይላችሁን ድፍረት እና የመመከት ብቃት እንዲሁ" ብለዋል ብሊንከን።

እናም በየቀኑ እያየን ነው። ይሁን እንጂ የዩክሬንን ሕዝብ አስደናቂ ቆራጥነት እና የመቋቋም ችሎታ፤ እንዲሁም የፀጥታ ኃይላችሁን ድፍረት እና የመመከት ብቃት እንዲሁ"

ዘለንስኪ በበኩላቸው ኃይሎቻቸው ዩክሬይንን ከሩሲያ የሚሳይል እና የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት በመከላከሉ ረገድ፡ ወሳኝ የሆኑትን የአየር መከላከያ መሣሪያዎች ጨምሮ ዩናይትድ ስቴትስ ለአገራቸው እየሰጠች ስላለው ድጋፍ አመስግነዋል።

በተያያዘም ዘለንስኪ እና ሌሎች የዩክሬን ባለሥልጣናት የአገራቸውን የአየር መከላከያ ይበልጥ ለማጠናከር በያዙት ጥረት እንዲያግዟቸው ዩናይትድ ስቴትስን እና አውሮፓውያን አጋሮቻቸውን ተማጽነዋል።

በተያያዘ የባይደን አስተዳደር ለእስራኤል ከሚሰጠው ድጋፍ እና ለዩናይትድ ስቴትስ የድንበር ደህንነት ጥበቃ ከሚያውለው የገንዘብ ወጭ ጋር በአሥር ቢሊዮኖች የሚሰላ አዲስ የእርዳታ ገንዘብ እንዲፈቅድ የዩናይትድ ስቴትስን ምክር ቤት ጠይቋል። ሆኖም ውጥኑ ከዩናይትድ ስቴትስ የድንበር ደህንነት ጥበቃ ጋር በተያያዘ ሌሎች ተጨማሪ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ከሚጠይቁ አንዳንድ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት በኩል ተቃውሞ ስለገጠመው እስካሁን ሊሳካ ያለመቻሉ ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG