በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ፕሬዚደንት ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ንግግር ያደርጋሉ


የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ
የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ

የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ዛሬ ለዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት ንግግር ያደርጋሉ፡፡

ፕሬዚደንቱ ንግግር የሚያደርጉት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ዩክሬን የሩስያን ወረራ ለመመከት የሚረዳትን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ባፋጣኝ እንዲፈቅድ ኋይት ሐውስ በመወትወት ላይ ባለበት በዚህ ወቅት ነው፡፡

የዩክሬን መሪ የተጋበዙት የምክር ቤት አባላት በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ዕርዳታ ባካተተው ረቂቅ ህግ ላይ አባላቱ ድምጽ ከመስጠታቸው አስቀድሞ በሚደረግ ዝግ ስብሰባ ላይ በቪዲዮ አማካይነት ቀርበው እንዲናገሩ መሆኑን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የብዙሐን መሪ ሴኔተር ቸክ ሹመር አመልክተዋል፡፡ ይህም “በሀገራቸው ላይ ስለተደቀነው አደጋ ከራሳቸው በግልጽ በቀጥታ ለመስማት መሆኑን ሴነተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የሥራ አመራር እና የበጀት ቢሮ ዳይሬክተር ሻላንዳ ያንግ ትናንት ሰኞ ለምክር ቤት አባላት በላኩት ደብዳቤ ይህ የአውሮፓ 2023 ዐመተ ምሕረት ካለቀ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ እና ሌላም ዕርዳታ የምታውለው ገንዘብ እንደማይኖራት ገልጸው አስጠንቅቀዋል፡፡ የባይደን አስተዳደር ለዩክሬን፡ ለእስራኤል እና ለለዩናይትድ ስቴትስ ድንበር ጥበቃ ያዘጋጀውን ወደ 106 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ግዙፍ የበጀት ዕቅድ ለምክር ቤት ያቀረበው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG