በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስረኞች ልውውጥ የተፈታው አሜሪካዊ ለዩክሬን ሲዋጋ ቆሰለ


የቀድሞ የባሕር ኃይል አባል ትሬቨር ሪድ
የቀድሞ የባሕር ኃይል አባል ትሬቨር ሪድ

ባለፈው ዓመት፣ አሜሪካ ከሩሲያ ጋራ ባደረገችው የእስረኞች ልውውጥ የተለቀቀው የቀድሞ የባሕር ኃይል አባል ትሬቨር ሪድ፣ ለዩክሬን ተሰልፎ ከሞስኮ ኃይሎች ጋራ ሲዋጋ እንደቆሰለ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ቪዳንት ፓቴል፣ ጉዳት የደረሰበት ሪድ፣ ለሕክምና ወደ ጀርመን እንደተወሰደ ተናግረዋል፡፡

ሪድ በጦርነቱ የተሰለፈው፣ የዩናይትድ ስቴትስን መንግሥት ወክሎ እንዳልኾነ፣ ቃል አቀባዩ አክለው ገልጸዋል፡፡

በሩሲያ ቁጥጥር ሥር የነበረው ሪድ የተለቀቀው፣ ባለፈው ዓመት በአደገኛ ዕፅ ዝውውር፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ታስሮ በነበረው የሩሲያ ፓይለት ምትክ በተደረገው የእስረኞች ልውውጥ ነበር፡፡

ይኹን እንጂ ሪድ፣ በሩሲያ - ዩክሬን ጦርነት፣ ጠመንጃ ለማንሣት መወሰኑ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሞስኮ የተያዙ ሌሎች ሁለት አሜሪካውያን እስረኞችን ለማስለቀቅ የምታደርገውን ጥረት እንዳያወሳስበው ስጋት ፈጥሯል፡፡

ሁለቱ አሜሪካውያን፣ የዎል ስትሪት ጆርናሉ ዘጋቢ ኢቫን ጌርስኮኾቪች እና የድርጅት ደኅንነት ሥራ አስፈጻሚው ፖል ዌለን እንደኾኑ ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG