በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በኪቭ እና ኦዴሳ የሚገኙ ዒላማዎችን አጠቃች


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዜለነስኪ
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዜለነስኪ

የሩሲያ ኃይሎች፣ በደቡባዊ ዩክሬን ኦዴሳ ግዛት፣ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የአየር ጥቃት ማካሔዳቸውን፣ ዋና ከተማዪቱን ኪቭ እና ሌሎች አካባቢዎችንም ዒላማ ማድረጋቸውን፣ የዩክሬን ባለሥልጣናት፣ ዛሬ ረቡዕ ተናግረዋል፡፡

የዩክሬን አየር ኃይል፣ ሩሲያ ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከተኮሰቻቸው 63 ሚሳየሎች እና ከላከቻቸው ድሮኖች መካከል፣ 37ቱን መትተው እንደጣሉ አስታውቋል፡፡

ሩሲያ ዋና ዒላማ ያደረገቻቸው፣ በኦዴሳ እና አካባቢው ያሉ መሠረተ ልማቶችንና ወታደራዊ ተቋማትን እንደኾነም አየር ኃይሉ ገልጿል፡፡

የኦዴሳ ወደብ፣ ሩሲያ፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ፥ የዩክሬንን እህል ከወደቡ ወደ ዓለም ገበያ የመጫን ስምምነቱን እንዳቋረጠች ከማስታወቋ በፊት፣ ለአንድ ዓመት ያህል፣ እህሉ ወደ ውጭ የሚላክበት እንደነበር ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዜለነስኪ፣ ዛሬ ረቡዕ በሰጡት መግለጫ፣ የሩሲያው የቅርብ ጊዜ ጥቃት፣ ዒላማ ያደረገው፥ የስምምነቱን የእህል መተላለፊያ መሠረተ ልማቶች ብቻ አይደለም፤ በመላው ዓለም፣ መደበኛ እና ሰላማዊ ሕይወት መኖር የሚፈልገውን እያንዳንዱን ሰው ጭምር ነው፤ ብለዋል፡፡

ዜሌነስኪ እንደገለጹት፣ ሩሲያ ከስምምነቱ መውጣቷን ተከትሎ፣ መንግሥታቸው፣ “የዩክሬንን ዓለም አቀፍ የምግብ ደኅንነት ዋስትና ሰጭነት ሚና፣ የመርከቦቻችንን የዓለም ገበያ ተደራሽነት፣ እንዲሁም በወደቦች እና በግብርና ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉትን ሥራዎች ለማስጠበቅ እየሠራ ነው፤” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG