በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን የሩስያን መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ማክሸፏን አስታወቀች


የብሔራዊ ጥበቃ ክፍል አገልግሎት ሰጭ በሥራ ላይ 6/1 /2023
የብሔራዊ ጥበቃ ክፍል አገልግሎት ሰጭ በሥራ ላይ 6/1 /2023

የዩክሬን ባለሥልጣናት፣ ዛሬ፣ በዋና ከተማዪቱ ኪየቭ ላይ የተነጣጠሩ፣ ከ30 በላይ የሩስያ ሚሳኤሎችንና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትተው መጣላቸውን ተናገሩ።

የዩክሬን አየር ኃይል፣ ዛሬ ዐርብ በሰጠው መግለጫ፣ በሩስያ የተተኮሱ 15 ክሩዝ ሚሳኤሎች እና ለጥቃት የተሠማሩ 21 ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ በአየር መከላከያ ሥርዐታቸው ተመትተው መክሸፋቸውንና መውደቃቸውን አስታውቋል። ኾኖም፣ በጥቂቱ ሁለት ሰዎች፣ በፍርስራሾቹ መቁሰላቸውን፣ ባለሥልጣናቱ አክለው ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና፣ ትላንት ኀሙስ፣ ኪየቭ ላይ በተነጣጠረ የሩስያ ሚሳኤል ጥቃት፣ አንዲት የዘጠኝ ዓመት አዳጊ እና እናቷን ጨምሮ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ፣ ሌሎች 16 መቁሰላቸውን፣ የዩክሬን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

እ.አ.አ በትላንቱ የሰኔ ወር መባቻ፣ በዓለም ዙሪያ በበርካታ ሀገራት፣ ታስቦ የዋለውን “የሕፃናት ቀን” መነሻ በማድረግ፣ በዕለታዊ ንግግራቸው ላይ አስተያየት የሰጡት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፣ “አሸባሪው መንግሥት፣ በዚኽ ቀን እንኳን፣ የአንድ ዩክሬናዊ አዳጊ ሕይወት ቀጥፏል፤” ሲሉ ተደምጠዋል።

በሌላ በኩል፣ የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ በዩክሬን ላይ የተደረገውን ወረራ አስመልክቶ፣ በዛሬው ዕለት ባወጣው የደኅንነት መረጃ፣ በአሁኑ ወቅት ሩሲያ፣ ድንበሯን በማጠናከር ወይም በኃይል በያዘቻቸው የዩክሬን ቦታዎች ጦሯን በማጎልበት መሀከል ስለምትወስደው ውሳኔ፣ በእጅጉ እያመነታች እንደኾነች አመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ትላንት ኀሙስ፣ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፣ አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ኪየቭ ወደሚገኝ መጠለያ መጠጋት ቢፈልጉም፣ ሥፍራዎቹ ተዘጉባቸው፤ በሚል በወጡ ዘገባዎች ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።

"መጠለያ ሥፍራዎቹ፥ ዘወትር ዝግጁ ኾነው እንዲገኙ ማድረግ፣ የየአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ልዩ ሓላፊነት እና ግዴታ ነው። ይህን ሓላፊነታቸውን ቸል ብለው ማየት በጣም ያማል። በእነርሱ ቸልታ ሰዎች ተጎድተው ማየት በጣም ያማል። ሓላፊነታቸውን ያልተወጡ ወገኖችን ለፍርድ የማቅረብ ቀጥተኛ ድርሻ፣ የሕግ አስከባሪ አካላት ነው።”

XS
SM
MD
LG