በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን ባክሙት ውጊያው ተባብሶ ቀጥሏል


ምስራቅ ዩክሬን ባክሙት አካባቢ
ምስራቅ ዩክሬን ባክሙት አካባቢ

ምስራቅ ዩክሬን የባክሙት አካባቢን ለመቆጣጠር ለወራት በዘለቀው ትግል በሁለቱም ወገኖች የሚካሄደው ከባድ ውጊያ ዛሬ ሰኞም መቀጠሉ ተነገሯል፡፡

የዩክሬን ጦር፣ ሩሲያ ከተማውን ለመያዝ የምታደርገውን ጥረት ለመመከት መድፎች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን እየተጠቀመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የብሪታኒያ መከላከያ ሚኒስቴር ባደረገው ግምገማ የሩሲያው ዋግነር ልዩ ወታደራዊ ቡድን አብዛኛውን የምስራቅ ባክሙት አካባቢዎች ሲቆጣጠሩ፣ የዩክሬን ኃይሎች ደግሞ የምስራቁን ክፍል መቆጣጠራቸውን አመልክቷል፡፡

የዋግነር መስራች ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ ሁኔታዎች አሰቸጋሪ መሆናቸውን ገልጸው ፣ በተለይ ጦራቸው ወደ ከተማው ማዕከላዊ ክፍል እየተጠጉ በሄዱ ቁጥር እጅግ ከባድ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ የዶናባስን ግዛት ለመቆጣጠር ላላት አጠቃላይ ግብ ባክሙትን መቆጣጠር እንደ ቁልፍ ኢላማዋ አድርጋ መያዝዋ ተመልክቷል፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ ባክሙትን እንደሚመክቱ ቃል ገብተዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን እና የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄንስ ስቶትልነበርግ ጉዳዩን በጥንቃቄ ቢመለከቱም በዚህ ግንባር ዩክሬን ብትሸነፍ የጠቅላላውን ጦርነት ውጤት የሚያመለክት አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG