በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተዋጊ ጄቶችን ለዩክሬን የማስታጠቁ ጉዳይ ዛሬ ፓሪስ ላይ ይነሳል


ፎቶ ፋይል፦ የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲ ሬዝኒኮቭ
ፎቶ ፋይል፦ የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲ ሬዝኒኮቭ

ለዩክሬን የተዋጊ ጀቶችን የማስታጠቁ ጉዳይ የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲ ሬዝኒኮቭ ከፈረንሳይ መሪዎች ጋር ዛሬ ፓሪስ ላይ በሚያደርጉት ስብሰባ እልባት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

የዩክሬን ባለሥልጣናት የሩሲያን ወረራው በተሻለ መንገድ ለመመከት የሚያስችላቸውን ተዋጊ ጀቶቻቸውን እንዲልኩላቸው ምዕራባውያን አጋሮቻቸውን የጠየቁ ቢሆንም ጥያቄዎቹ አሳስቢ ሆነዋል፡፡

ፈረንሳይ ለዩክሬን ተዋጊ ጀቶችን ትሰጥ እንደሆነ ትናንት የተጠየቁት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን “እንዳይሰጥ የተከለከለ ነገረ የለም” ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ “እንደዚያ ያሉ ውሳኔዎች ሲወሰኑ መታየት ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፣ ከእነዚህ መካከል መሳሪያዎቹ የሩሲያን ምድር ላይ የሚያርፉ መሆን የለባቸውም፣ ውጥረትን የሚያባብሱና የፈረንሳይን ጦር አቅም የሚያዳክሙ መሆን አይኖርባቸውም” ሲሉ ማክሮን አክለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም ባለፈው ሰኞ በዋይት ሀውስ ለዩክሬን ኤፍ 16 ተዋጊ ጀቶችን ይሰጡ እንደሆነ ከሪፖርተሮች ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ “አያይ!” (“No.”) የሚል ምላሽ ብቻ ነበር፡፡

ባላፈው ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ እና ለሳምንታት ስታንገራግር የቆየችው ጀርመን ዘመናዊ የሊዮፖርድ 2 ታንኮችን እንደሚሰጧት ቃል ከገቡ በኋላ፣ ዩክሬን በዚያ በኩል የቀናት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG