በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት ሩሲያ በዩክሬን ለሰራችው ወንጀል የምትከሰስበት ልዩ ፍ/ቤት ጠየቀ


የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደርሌይን
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደርሌይን

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደርሌይን ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ወንጀል የምትከሰስበት ልዩ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ጠየቁ፡፡

ቮንደር ሌይን ይህን የተናገሩት ሩማኒያ ውስጥ ስለጦርነቱና እንዲሁም የዩክሬን መርዳት ስለሚቻልበት ለመምከር ትናንት በተጀመረውና ዛሬ በተጠናቀቀው የኔቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ባሰሙት የመዝጊያ ንግግራቸው ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ቮን ደርሌይን ሩሲያ በወረራው የሰራቸውን ጥቃትና ወንጀል መርምሮ የሚከስ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ያቀረቡት ጥያቄ የተባበሩት መንግሥታትን ድጋፍ ማግኘቱም ተመልክቷል፡፡

የሩሲያ ኃይሎች ዩክሬን ከወረሩበት ካለፈው የካቲት ጀምሮ በዩክሬን ላይ ለደረሰው ውድመት መልሳ የምትቋቋምበትን ካሳ እንዲከፍሉ፣ ሩሲያ እና የአገዛዙ ከበርቴዎች መጠየቅ አለባቸው ሲሉ የጠየቁት ቮን ደር ሌይን “የሩሲያ ዘግናኝ ወንጀል ቅጣቱን ሳያገኝ አያልፍም” ብለዋል፡፡

የኔቶዋና ጸሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ዩክሬን አንድ ቀን የምዕራቡን ወታደራዊ ህብረት ትቀላቀላች ሲሉ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በቀጥታ የሚቃረን ንግግር ተናግረዋል፡፡

“የኔቶ በር ክፍት ነው” ባሉበት የትናንቱ ንግግራቸው፣ ዋና ጸሃፊው በቅርቡ የተቀላቀሉትን አባል አገራት ጠቅሰው ወደ ኔቶ መግባት በሚፈልጉ አገሮች ላይ ሩሲያ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት የላትም ሲሉ የዩክሬንን አባላትነት ጥያቄንም አስመልክቶ በዚያ አቋማችን እንጸናለን ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

“ፕሬዚዳንት ፑቲን አገሮች የራሳቸውን የሉዓላዊነት ውሳኔ እንዳያሳልፉ ፑቲን ሊከለክሉ አይችሉም” ያሉት ዋና ጸሃፊው “ፑቲን የሚፈሩት ዴሞክራሲና ነጻነትን ይመስለኛል ያ ለእርሳቸው ትልቁ ፈተና ነው” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG