በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በተወረርን ዘጠነኛ ወር በሩሲያ አልተሰበርንም” ዜሌንስኪ


 የዩክሬ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ
የዩክሬ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ

የሩሲያ ወረራ ዘጠነኛ ወሩን በያዘበት በትናንትናው ዕለት መልዕክት ያስተላለፉት የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ “ጠላት ሊሰብረን አልቻለም፣ እኛን ለመሥበር መንገዱን አያገኝም” ሲሉ ተደምጠዋል።

በስም ባልጠቀሷቸው ግንባሮች ዩክሬን ጥቃት ማቀዷንም በምሽት የቪዲዮ መልዕክታቸው አስታውቀዋል።

በሩሲያ ተደጋጋሚ የሚሳዬል ድብደባ የደረሰባት ዩክሬን አብዛኛው ክልሏ በኃይል እጦት ምክንያት በጨለማ የተዋጠ ሲሆን፣ አስተማማኝ የውሃ አቅርቦትም የለም። ሩሲያ የዩክሬንን ኃይል ማመንጫዎችና አገልግሎት ሰጪ መዋቅሮቿን ስትደበድብ ከርማለች።

ሩሲያ የኬርሶን ግዛት ላይ ቦምብ እያወረደች መሆኑን ዜለኤንስኪ ተናግረዋል። ሩሲያ በዘጠኝ ወራት የወረራ ቆይታዋ የተቆጣጠረቻት ብቸኛ ከተማ ስትሆን፣ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ጦሯ ከተማውን ለቆ ወጥቷል።

በየሰዓቱ በከተማዋ ላይ የአየር ድብደባ በመፈጸም ላይ መሆኗንና፣ በትናንትናው ዕለት ብቻ ሰባት ሲቪሎች ሲሞቱ 21 መቁሰላቸውን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ዩክሬን ገዢ ቦታዎችን መቆጣጠሯን የቀጠለች መሆኑንና ወደፊትም ለመቀጠል መዘጋጀቷን ዜሌንስኪ ጨምረው አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG