በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ አየር ጥቃት በዩክሬን የሆስፒታል ማዋለጃ ክፍልን መታ


ሚሳዬሉ ዛፕሮዥዢያ ውስጥ ቪልኒያንስክ በተባለች ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል የደረሰው ጥቃት
ሚሳዬሉ ዛፕሮዥዢያ ውስጥ ቪልኒያንስክ በተባለች ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል የደረሰው ጥቃት

ሩሲያ በምሽት የፈጸመችው የአየር ድብድባ አንድ የሆስፒታል ማዋለጃ ክፍልን ሲመታ አዲስ የተወለደ ሕጻን ሲሞት እናቲቱ ጉዳት ደርሶባታል ሲሉ የዩክሬን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታውቀዋል።

ሚሳዬሉ ዛፕሮዥዢያ ውስጥ ቪልኒያንስክ በተባለች ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ያለ ሁለት ፎቅ የማዋለጃ ሕንጻ ማውደሙን ባለሥልጣናቱ ጨምረው ገልጸዋል።

የአገሪቱ የአስቸኳይ ግዜ አገልግሎት በበኩሉ የሕጻኑን እናትና አንድ ዶክተርን ከሕንጻው ፍርስራሽ ውስጥ ማውጣቱን አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በቴሌግራም ባስተላለፉት መልዕክት ሩሲያ “ከሲሎችና ከሲቪል መገልገያዎች ጋር ጦርነቷን ቀጥላለች” ብለዋል።

“ጠላት በአገራችን ላይ ላደረሰው ሠይጣናዊ ሥራ ሁሉ ተጠያቂ ይሆናል” ብለዋል ዜሌንስኪ በመልዕክታቸው።

የአውሮፓ ፓርላማ ሩሲያን “መንግሥታዊ ሽብር ፈጻሚ” ብሎ መፈረጁን ዜሌንስኪ በደስታ ተቀብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት፤ ማክሰኞ የዩክሬን ባለሥልጣናት አንድ በኪየቭ የሚገኝን የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ገዳም ድንገት ፈትሸዋል። ፍተሻው በሩሲያ ልዩ ቡድን ሊደረግ የሚችልን የሰርጎ ገብ እንቅስቃሴን ለመመከት ነው ተብሏል።

በዩኔስኮ ድንቃ ድንቅ መዝገብ በሰፈረው ገዳም የተደረገው ፍተሻ አንድ ቄስ ስለ ሩሲያ መልካምነት በስብከታቸው ወቅት ማንሳታቸውን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።

በሞስኮብ የሚደገፈው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የፑቲንን ወረራ በብርቱ በመደገፉ በዩክሬን የሚገኙ የሃይማኖቱ ተከታዮች ግኑኝነታቸውን አቋርጠዋል።

በሞስኮብ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ “የዩክሬን ባለሥልጣናት በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ላይ ጦርነት አውጀዋል” ሲሉ ከሰዋል።

XS
SM
MD
LG