በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩሲያ የኃይል መሠረተ ልማት ድብደባ ዩክሬን በጨለማ ተዋጠች


ፎቶ ፋይል፦ ሩሲያ የኃይል መሠረተ ልማቶችን ከአየር መደብደቧን ተከትሎ፣ በሩስያ የሚሳኤል ጥቃት የተጎዳውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ የድንገተኛ የእሳት አደጋ ሠራተኞች እሳቱን የማጥፋት ሥራ እያከናወኑ፤ 10/18/2022
ፎቶ ፋይል፦ ሩሲያ የኃይል መሠረተ ልማቶችን ከአየር መደብደቧን ተከትሎ፣ በሩስያ የሚሳኤል ጥቃት የተጎዳውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ የድንገተኛ የእሳት አደጋ ሠራተኞች እሳቱን የማጥፋት ሥራ እያከናወኑ፤ 10/18/2022

ሩሲያ የኃይል መሠረተ ልማቶችን ከአየር መደብደቧን ተከትሎ፣ በበርካታ የሃገሪቱ ክልሎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ውስን እንደሚሆን መንግሥታዊ የሆነው የዩክሬን የኃይል ኩባንያ ኡከነርጎ አስታወቋል።

በምሽት የተፈፀመው ድብደባ በሃገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል የሚገኝን የኃይል ማከፋፈያ የጨመረ ሲሆን፣ በቀሩት ማከፋፈያዎች ላይ ጫና እንዳይበዛና የወደሙትን ማከፋፈያዎች ለመጠገን የኤሌክትሪክ አጠቃቀም ቁጠባ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብሏል ኡከነርጎ።

በክሪሚያ የሚገኙ በሩሲያ የተሾሙ ባለሥልጣን ዛሬ እንዳሉት በምሽት የተፈፀመው የድሮን ጥቃት በቦታው የሚገኝና ሙቀትን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚቀይርን ጣቢያ ኢላማ አድርጎ ነበር። ባለሥልጣኑ ጨምረውም፣ በክሪሚያ የሃይል ችግር እንደሌለና በድብደባው በሰው ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ተናግረዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ትናንት የሃገሪቱ ስልታዊ የኑክሌር ኃይል ልምምድ ሲያደርግ ከርቀት ተመልክተዋል። ይህም ከፍተኛ የኑክሌር ጥቃት ቢደርስባት እንዴት አድርጋ ሩሲያ መልስ እንደምትሰጥ የተለማመዱበት ነው ተብሏል።

የሩሲያ መንግሥት ቴሌቭዥን ፑቲን ልምምዱን ከርቀት በቪዲዮ ሲከታተሉና ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችም ስለልምምዱ መግለጫ ሲሰጡ አሳይቷል።

ሩሲያ “መብረቅ” በመባል የሰየመችውን ዓመታዊ ልምምድ እንደምታደርግ አስታውቃ ነበር ሲል ዋይት ሃውስ ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ አመልክቶ ነበር። ሩሲያ የኑክሌር ልምምዷን ያካሄደችው የመጣው የሰሜን አእትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) አእባል ሀገራት “ብርቱ ወይም ጽኑ ቀትር” ሲል የሚጠራውን የኑክሌር ልምምድ በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት ነው።

ትናንት፤ ረቡዕ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የእስራኤሉን ፕሬዚዳንት አይሳክ ሄርዞግ በዋይት ሃውስ ተቀብለው አነጋግረዋል። አይሳክ ሄርዞግ በሩሲያ ጥቅም ላይ የዋሉትን የኢራን ድሮኖች በተመለከተ ሃገራቸው ያላትን መረጃ ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እንደሚያካፍሏቸው አመላክተው ነበር።

የሄርዞግ ቢሮ እንዳለው በዩክሬን ጥቅም ላይ የዋሉትንና ባለፈው ዓመት በኢራን የተሞከሩትን ድሮኖች ተመሳሳይነት የሚያሳዩ ፎቶዎች እስራኤል አላት።

ዩክሬንና የምዕራብ አጋሮቿ ሩሲያ የዩክሬን መዲና ኪቭን ጨምሮ ለመደብደብ የተጠቀመችባቸው ድሮኖች ኢራን ሠር የሆኑ ሻሂድ-136 የተባሉ ድሮኖች መሆናቸውን ሲናገሩ ሰንብተዋል።

XS
SM
MD
LG