በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ መርማሪዎች በኒዩክለር ተቋሙ ሥራቸውን ሊጀመሩ ነው


ዩክሬን ዛፖሮዥዢያ የሚገኘውን የኒዩክርለ ኃይል ማመንጫ ተቋም
ዩክሬን ዛፖሮዥዢያ የሚገኘውን የኒዩክርለ ኃይል ማመንጫ ተቋም

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ መርማሪዎች ዩክሬን ዛፖሮዥዢያ የሚገኘውን የኒዩክርለ ኃይል ማመንጫ ተቋም የመመልከት ሥራቸውን ዛሬ ሐሙስ ይጀመራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

መርማሪዎቹ፣ በአካባቢው የሚካሄደው ጦርነት፣ ተቋሙን ለአደጋ ሊያጋልጠው ይችላል የሚለውን፣ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሥጋትና ደህንነት ጉዳዮች እንደሚገመግሙም ተነገሯል፡፡

የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤነርጂ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ ለሪፖርተሮች በሰጡት መግለጫ፣ በተቋሙ አቅራቢያ “ዛሬ ጧትን ጨምሮ ወታደራዊ እንቅስቃሴው አይሏል” ብለዋል፡፡

“ይሁን እንጂ ጥቅምና ጉዳቱ በማመዛዘን እዚህ ከደረሰን በኋላ ሥራውን አናቆምም” በማለት አክለዋል ግሮሲ፡፡

ዩክሬንና ሩሲያ በአውሮፓ ትልቁና በዩክሬን ደግሞ ቁልፍ የኃይል ምንጭ ወደ ሆነው የኒዩክለር ተቋም አቅራቢያ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ተኩሰዋል በሚል እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ይህ ክስ፣ ዛሬ ሀሙስም የቀጠለ ሲሆን፣ ሩሲያ፣ ዩክሬን ተቋሙን ለመያዝ ወታደራዊ ቡድኖችን ልካለች ስትል፣ ዩክሬን ደግሞ፣ የሩሲያ ኃይሎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ መርማሪዎቹ ወደ ተቋሙ የሚጓዙበትን አቅጣጫ በከባድ መሳሪያ እየደበደቡ ነው ብለላች፡፡

XS
SM
MD
LG