በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን ሩሲያ የያዘችውን ቦታ ደበደበች


ዩክሬን በደቡባዊ ግዛቷ ኼርሶን ውስጥ በፈፀመችው የሮኬት ድብደባ ከተጎዳው የመኖሪያ ሕንፃ ውስጥ የነፍስ አድን ሰራተኞች ከአደጋ የተረፈውን ሰው ሲታደጉ።
ዩክሬን በደቡባዊ ግዛቷ ኼርሶን ውስጥ በፈፀመችው የሮኬት ድብደባ ከተጎዳው የመኖሪያ ሕንፃ ውስጥ የነፍስ አድን ሰራተኞች ከአደጋ የተረፈውን ሰው ሲታደጉ።

ዩክሬን ሩሲያ በተቆጣጠረችው ደቡባዊ ግዛቷ ኼርሶን ውስጥ ስለፈፀመችው የሮኬት ድብደባ የሁለቱም ወገኖች ባለሥልጣናት የተለያየ ይዘት ያላቸውን መግለጫ እየሰጡ ናቸው።

ዩክሬን ባለሥልጣኖች “ኖቫ ካኾቭካ በሚባለው አካባቢ የሚገኝ የሩሲያ የጦር መሣሪያ ማከማቻ በረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሮኬት መትተን 52 የሩሲያ ወታደሮችን ገድለናል” ሲሉ ሩሲያዊያኑ ግን ሮኬቱ የወደቀው በሲቪል የልማት መዋቅሮች ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ “የሩሲያ ኃይሎች ምሥራቅ ዩክሬን ዶኔትስክ ክፍለ ሃገር ውስጥ ተጨማሪ ቦታዎችን መያዛቸውን ቀጥለዋል” ሲል የብሪታንያ የመከላከያ ሚኒስቴር ተናግሯል።

ሩሲያ በዩክሬን ኃይሎች ላይ ጫናዋን እያበረታች ለቀጣይ ጥቃት ጦሯን እያደራጀች ሳትሆን እንደማትቀር የብሪታኒያው መግለጫ አመልክቷል።

በተያያዘ ዜና ሩሲያ በዶኔትስክ ክፍለ ግዛት ቻሲቭ ያር ከተማ ትናንት ሚሳይል ተኩሳ በመታችው የመኖሪያ ህንፃ ውስጥ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ወደ 34 ከፍ ማለቱን የአካባቢው ባለሥልጣናት የገለፁ ሲሆን ከፍርስራሹ ሥር ዘጠኝ ሰዎችን በህይወት ማውጣታቸውን ገልፀዋል።

ቻሲቭ ያር ከተማ ባለፈው ሳምንት ሉሃንስክን የተቆጣጠሩት የሩሲያ ኃይሎች ዋና ዒላማ ከሆነችው ከክራማቶርስክ ከተማ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት እንደምትገኝ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG