በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜሌንስኪ የሚሳይል መከላከያ መሣሪያ ዕርዳታ ተማፀኑ


ክሬሜንቹክ በተባለች ከተማ በሚገኘው የገበያ ማዕከል በደረሰው የሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት የዩክሬን ባለሥልጣናት በርካታ ሲቪሎች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል የሚል ሥጋት አላቸው፤ እአአ ሰኔ 27/2022
ክሬሜንቹክ በተባለች ከተማ በሚገኘው የገበያ ማዕከል በደረሰው የሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት የዩክሬን ባለሥልጣናት በርካታ ሲቪሎች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል የሚል ሥጋት አላቸው፤ እአአ ሰኔ 27/2022

ከሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት ዋና ፀሃፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ ጋር የተወያዩት የሩሲያን ሽብርተኛ ጥቃት ለመከላከል ጠንካራ የሚሳይል መከላከያ መሳሪያ ያስፈልገናል ሲሉ አጥብቀው አሳሰቡ።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ከኔቶ ዋና ፀሃፊ ጋር የተወያዩት ስፔይን ማድሪድ ላይ የሚካሄደው የቃል ኪዳን ድርጅቱ የመሪዎች ጉባዔ ከመከፈቱ አስቀድሞ ሲሆን ጉባዔው ከሚነጋገርባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች መካከል አንዷ ዩክሬን እንደምትሆን ይጠበቃል።

ስቶልትንበርግ ከዜሌንስኪ ጋር ከተወያዩ በኋላ በትዊተር ባወጡት ጽሁፍ "በመሪዎቹ ጉባዔአችን ላይ ለቅርብ አጋራችን ለዩክሬን የምንሰጠውን ዕርዳታ አሁንም ወደ ፊትም ከፍ አድርገን እንቀጥላለን" ብለዋል።

የሩሲያ ኃይሎች ትናንት ሰኞ አንድ የገበያ አዳራሽ በሚሳይል መትተው ቢያንስ አስራ ስምንት ሰዎች ገድለዋል። ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ ክሬሜንቹክ በተባለች ከተማ በሚገኘው የገበያ ማዕከል ውስጥ ሆን ተብሎ ተነጣጥሮ የተፈጸመ ያሉት ጥቃት በደረሰበት ወቅት ከአንድ ሺ የሚበልጡ ሰዎች እንደነበሩ ገልጸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንክን በትዊተር ባወጡት ቃል የዛሬው ሰው በበዛበት የገበያ ማዕከል ላይ የደረሰው ጭካኔ የተመላበት የሚሳይል ጥቃት ዓለምን እጅግ አስደንግጧል ብለዋል። በማስከተልም ከዩክሬን ጎን መቆማችንን እንቀጥላለን ሩሲያንን እና ይህን ጨካኝ አድራጎት የፈጸሙትን ተጠያቂ እናደርጋለን ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ ጥቃቱን አውግዘው የድርጅቱ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ዩክሬይን የሚሳይል ጥቃቱን ተከትሎ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ዛሬ ተሰብስቦ እንደሚነጋገር አስታውቀዋል።

ሩሲያ የሚሳይል ጥቃቱን ያደረሰችው የቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች በጀርመን ቢቫሪያን አልፕስ ጉባዔ ላይ ሳሉ ሲሆን መሪዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ በዚህ የጭካኔ ጥቃት ለጠፋው የንጹሃን ህይወት ከዩክሬን ህዝብ ጋር አብረን እናዝናለን ብለዋል።

XS
SM
MD
LG