በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን እና ሩሲያ ኃይሎች ለሲቪሮዶኔትስክ 'እያንዳንዷ ስንዝር መሬት' እየተዋጉ መሆናቸውን ዘለንስኪ ገለፁ


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የዩክሬን እና የራሽያ ሀይሎች በሲቪሮዶኔትስክ ለሚገኘው እያንዳንዷ ስንዝር መሬት እየተዋጉ መሆናቸውን ገልፀው፣ ዩክሬን ዘመናዊ የሚሳይል መቃወሚያ ሥርዓት ያስፈልጋታል ሲሉ ዓለም አቀፍ አጋሮችን ተማፅነዋል።

ዘለንስኪ ምሽቱን በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት የሩሲያ ቁልፍ ኢላማ አለመቀየሩን እና በሲቪሮዶኔትስክ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ወደሚገኙት ሊሲቻንስክ፣ ባከሙት እና ስሎቭያንስክ ከተሞች እየገፉ በሆኑን ተናግረዋል።

የዘለንስኪ አማካሪ ሚኻይሎ ፖዶሊያክ ሰኞ እለት ባስተላለፉት የትዊተር መልዕክት "ጦርነቱን ለማስቆም ከፍተኛ የጦር መሳሪያዎች ያስፍለጉናል" በማለት የሚያስፍለጉዋቸውን የመሳሪያ አይነቶች እና ብዛት በዝርዝር አስፍረዋል። የመከላከያ ሚኒስትር ወኪሎች ረቡዕ እለት በብራስልስ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ በመግለፅም ውሳኔያቸውን እንደሚጠባበቁ አስታውቀዋል።

በሁለቱም ወገኖች በኩል እየደረሰ ያለውን ጉዳት ማረጋገጥ ባይቻልም በሩሲያ በኩል የሟቾች ቁጥር ከ40 ሺህ እንደሚበልጥ ዘለንስኪ በዚህ ወር ገልፀው ነበር።

የእንግሊዝ መከላከያ ሚኒስቴር በቅርብ ቀናት በሲቪሮዶኔትስክ እየተደረገ ያለው ውጊያ የሚያስቆጣ መሆኑን በመግለፅ ሩሲያ ወንዝ አቋራጭ ውጊያዎችን የማካሄድ አቅሟ በቀጣይ ጦርነቱ ላይ ትልቅ ሚና የሚጫወት ይሆናል ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ሎይድ ኦስቲን በኔቶ ዋና መቀመጫ ስብሰባ እያካሄዱ ሲሆን ባለፈው ግንቦት ወር በድህረገፅ አማካኝነት የተካሄደውን የኔቶ ስብሰባ ተከትሎ ዩክሬን በጦር ሜዳ የሚያካሂደውን እንቅስቃሴ አጠናክራ እንድትቀጥል ከዩክሬን ጋር ያለንን ጥምረት የበለጠ ለማስፋት እየጣርን ነው ብለዋል።

ሩሲያ በአሁኑ ወቅት 97 ከመቶ የሚሆነውን የሉሃንስክ ግዛት መቆጣጠሯን ብታስታውቅም አብዛኛውን የዶምባስ ምስራቃዊ ክፍል ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት የኢንዱስትሪ ማዕከል የሆነችው ሲቮሮዶኔትስክ ትልቅ ሚና ይኖራታል።

XS
SM
MD
LG