በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ኪየቭ ላይ የአየር ጥቃት አደረሰች


ፎቶ ፋይል፦ የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ በሮኬት ጥቃት የደረሰውን ጉዳት እየተመለከቱ በኪየቭ፣ ዩክሬን እ አአአ ጥር 2/2024
ፎቶ ፋይል፦ የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ በሮኬት ጥቃት የደረሰውን ጉዳት እየተመለከቱ በኪየቭ፣ ዩክሬን እ አአአ ጥር 2/2024

ሩሲያ ዛሬ ሐሙስ ዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት አድርሳለች፡፡ የዩክሬን የአየር ኃይል ከሩሲያ የተተኮሱትን ሠላሳ አንዱንም ሚሳይሎች መተትን ጥለናል ሲል አስታውቋል፡፡

የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ የሮኬት ፍንጥርጣሪዎች በከተማው የተለያዩ ቦታዎች መውደቃቸውን እና የመኖሪያ ህንጻዎች መምታታቸውን ገልጸዋል፡፡ በብዙ አካባቢዎች የእሳት ቃጠሎ ማስነሳታቸውንም አክለው አመልክተዋል፡፡ ከንቲባው እንዳሉት ቢያንስ አስር ሰዎች ተጎድተዋል፡፡

ዛሬ በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው “የሽብር አድራጎቱ ቀን እና ሌሊት እንደቀጠለ ነው” ያሉት የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ “አጋሮቻችን በተለይ የአየር ጥቃት መከላከያ መሣሪያ እርዳታ ይላኩልን” ሲሉ ተማጽነዋል፡፡

ሩሲያ ኪየቭ ላይ ጥቃቱን ያደረሰችው የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ የኋይት ሐውስ የብሄራዊ ጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቫንን ተቀብለው ባነጋገሩ ማግሥት መሆኑ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ሩሲያ ወርራ በተቆጣጠረቻቸው የዩክሬይን አካባቢዎች ነዋሪዎችን በፍርሃት እያሸማቀቀች መሆኗን አመለከተ፡፡ ከ2300 የሚበልጡ ሰለባዎችና ዕማኞችን በማነጋገር የተጠናቀረው ሪፖርት የሞስኮ ኃይሎች ሕዝቡን የሩስያ ቋንቋ እንዲናገር እያስገደዱት ዩክሬናዊ ማንነቱንና ባሕሉን እንዳያሳይ እያፈኑት መሆናቸውን አውስቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG