በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩሲያ በተያዙ የዩክሬን ግዛቶች የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ በመሰጠት ላይ ነው


በሩሲያ በተያዙ የዩክሬን ግዛቶች ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ዛሬ በመሰጠት ላይ ነው።
በሩሲያ በተያዙ የዩክሬን ግዛቶች ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ዛሬ በመሰጠት ላይ ነው።

በሩሲያ በተያዙ የዩክሬን ግዛቶች ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ዛሬ በመሰጠት ላይ ነው። ሕዝበ ውሳኔው ነዋሪዎቹ አካባቢያቸው ከሩሲያ ጋር እንዲቀላቀል ይፈልጉ እንደሆን ይጠይቃል።

ዛሬ ድምፅ የተጀመረባቸው ቦታዎች ሉሃንስክ፣ ኬርሶን እና በከፊል በሩሲያ ቁጥጥር ስር ባለችው ዛፖሪዢዢያ እንዲሁም ዶነትስክ ክልሎች ነው።

ሕዝበ ውሳኔው ሩሲያ ቦታዎቹን ገንጥላ ለመቀላቀልና ሕጋዊ ለማስመሰል ያደረገችው ነው በሚል የምዕራቡ ዓለም በማውገዝ ላይ ይገኛል።

የጸጥታና ትብብር ድርጅት በአውሮፓ የተሰኘው ተቋም ሕዝበ ውሳኔው ሕገወጥ ነው ብሏል።

የዛሬው ሕዝበ ውሳኔ እይተካሄደ ያለው ከሁለት ቀናት በፊት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን 300 ሺህ የሚሆኑ የሀገራቸውን ተጠባባቂ ወታደሮች “ለልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” በከፊል እንደሚያንቀሳቅሱ ካሳወቁ በኋላ ነው።

የዩክሬንን መልሶ ማጥቃትና ይዞታዎችን መልሶ መቆጣጠርን ተከትሉ ፑቲን ሰሞኑን በቴሌቭዥን ባደረጉት ጥሪ፣ ተጠባባቂ ሃይላቸውን መጠቀም የሩሲያን ግዛትና ሉአላዊነት ለማስከበር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ፑቲን በመልዕክታቸው የምዕራቡ ዓለም ሩሲያን ለማዳከምና ለማውደም መነሳቱን በመጠቆም “ሩሲያንና ሕዝቧን ለመከላአከል በእጃቸን የሚገኘውን ማንኛውንም አማራጭ እንጠቀማለን” ብለዋል፡፡

ጥሪውን በመቃወም በሞስኮና በሌሎች የሩሲያ ከተሞች ተቃውሞ በመደረግ ላይ ሲሆን ፖሊስ ወደ 1ሺ 300 የሚሆኑ ተቃዋሚዎችን ይዟል።

የእንግሊዝ የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ በለቀቀው መረጃ ባለፉት ሦስት ቀናት የዩክሬን ሃይሎች ጠንካራ ይዞታዎችን በበርካታ ቦታዎች መቆጣጠራቸውን ይፋ አድርጓል።

XS
SM
MD
LG