በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ጦር ዛሬም የዩክሬንን ከተሞችን ደበደቡ፣ የሰብዓዊ መተላለፊያ ኮሪደሮች እንከፍታለን አሉ


የዩክሬን ወታደር በኪየቭ፣ ዩክሬን ዳርቻ የሚገኘውን የኢርፒን ወንዝ አረጋዊያንን ለማሻገር እርዳታ ሲሰጡ እ አ አ መጋቢት 7/2022
የዩክሬን ወታደር በኪየቭ፣ ዩክሬን ዳርቻ የሚገኘውን የኢርፒን ወንዝ አረጋዊያንን ለማሻገር እርዳታ ሲሰጡ እ አ አ መጋቢት 7/2022

የሩስያ ኃይሎች በዛሬው ዕለት ደቡባዊ እና ሰሜናዊ የዩክሬይን ከተሞችን በቦምብ መደብደባቸው ተገለጠ። በኃይል ወደ ኪየቭ ለመግባት ሳያቅዱ እንዳልቀሩም የዩክሬይን ወታደራዊ ባለሥልጣናት እየተናገሩ ነው።

የዩክሬን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሲናገሩ የሩስያ ኃይሎች ትኩረት ኪየቭን፣ ካርኬቭን፣ ቼርኒሂቭን፣ ሱሚን እና ሚኮላይቭን መክበብ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው ሰኞ የወጣ አንድ መግለጫ ሩሲያ ሲቪሎች ላይ የአየር ድብደባ በመፈጸም እና በያዘቻቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ ቀውስ በመፍጠር ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህጎች ጥሳለች ሲል ከሷል።

XS
SM
MD
LG