በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ሮኬቶችንና የመድፍ ጥይቶችን ከሰሜን ኮሪያ ልትገዛ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሠራተኞች ፓርቲ ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ 6/23/2022
ፎቶ ፋይል፦ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሠራተኞች ፓርቲ ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ 6/23/2022

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዩክሬን ውስጥ በማካሄድ ላይ ለሚገኘው ውጊያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሮኬቶችንና የመድፍ ጥይቶችን ከሰሜን ኮሪያ ለመግዛት በሂደት ላይ መሆኑን በዩናይትድ ስቴትስ የመረጃ ተቋም ዝቅተኛ ደረጃ የተሰጠው አንድ አዲስ መረጃ አመልክቷል፡፡

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን “ሩሲያ ፊቷን ወደ ተገለለችው ሰሜን ኮሪያ ማዞሯ፣ የሩሲያ ጦር በማዕቀቡና በመሳሪያ ቁጥጥር የተነሳ በዩክሬን ከፍተኛ የጦር መሳሪያ አቅርቦት ችግር እየገጠመው መሆኑን ያሳያል” ማለታቸውን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ሩሲያ ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎችን ከሰሜን ኮሪያ ትፈልጋለች ብለው እንደሚያምኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ የመሳሪያዎቹ መጠን ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል ባለሥልጣናቱ አልገለጹም፡፡

መረጃዎቹ የተገኙት የባይደን አስተዳደር በቅርቡ፣ የሩሲያ ጦር በዩክሬን ለሚያካሂደው ጦርነት ኢራን ስሪት የሆኑ ድሮኖችን ባለፈው ነሀሴ መረከቡን ካረጋገጡ በኋላ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ዋይት ኃውስ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ሩሲያ ከቴህራን የወሰደቻቸው ድሮኖች የቴክኒካል እክል የገጠማቸው መሆኑን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG