ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን በአሁኑ ወቅት ሞስኩ ይገኛሉ።
ጉብኝታቸው የሚያተኩረው ሩሲያ ለሦሪያው ፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ የምትሰጠውን ድጋፍ መቀጠሏን አስመልክቶ ከሩሲያው አቻቸው ሴርጌ ላቭሮቭ ጋር በሚያደርጉት ንግግር ላይ ይሆናል።
ሦሪያ ባለፈው ሳምንት በራሷ ሲቪሎች ላይ የኬሚካዊ ጦር መሣሪያ ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ የሰጠችው ወታደራዊ ምላሽ በፕሬዘዳንት ትራምፕ አስተዳደር የሩሲያና ዩናይትድ ስቴትስን ትብብር ለማቀራረብ የነበረውን ተስፋ ሊያወሳስብ እንደሚችል ይገመታል።
በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ሲንዲ ሴይን ሪፖርት ሰሎሞን ክፍሌ ያቀርበዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ