በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ከሩሲያ ጋር የእሥረኛ ልውውጥ ለማድረግ ሃሳብ አቀረበች


ፎቶ ፋይል፦በሩሲያ እስር ላይ የሚገኙት በሰላይነት ወንጅላ የታሰረው ፖል ዊላንን፣ አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ኮከብ ተጫዋች ብሪትኒ ግራይነርን
ፎቶ ፋይል፦በሩሲያ እስር ላይ የሚገኙት በሰላይነት ወንጅላ የታሰረው ፖል ዊላንን፣ አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ኮከብ ተጫዋች ብሪትኒ ግራይነርን

ዩናይትድ ስቴትስ ለሩሲያ "ትልቅ ሃሳብ" አቅርበንላታል" ስትል ትናንት ረቡዕ ነው ያስታወቀችው። ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች እንዳሉት ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችው ዕቅድ ተፈርዶባቸው እስር ላይ የሚገኙትን ሩሲያዊ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪ ቪክተር ቡትን ወደሞስኮ መልሳ በመላክ አሜሪካዊቱን የቅርጫት ኳስ ኮከብ ተጫዋች ብሪትኒ ግራይነርን እና ሩሲያ በሰላይነት ወንጅላ ያሰረቻቸውን ፖል ዊላንን ለማስለቀቅ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ሀሳቡን ያቀረበችው ባለፈው ሰኔ ወር ከበርካታ ሳምንታት በፊት ሲሆን ሁለቱ መንግሥታት በጉዳዩ ዙሪያ የተነጋገሩበት ቢሆንም እስካሁን ምንም ውጤት እንዳላመጣ ተገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንክን ስለቀረበው የእሥረኛ ልውውጥ ዕቅድ ዝርዝር ውስጥ ሳይገቡ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል በዚሁ ሳምንት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭን በስልክ ሲያነጋገሩ ጉዳዩን እንደገና እንደሚያነሱባቸው አመልክተዋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በእስረኛ ልውውጡ ጉዳይ ድርድሩ መቀጠሉን ነገር ግን እስካሁን ስምምነት ላይ አለመደረሱን ዛሬ አስታውቀዋል።

በየካቲት ወር ሻንጣዋ ውስጥ በብልቃጥ በዘይት መልክ የተቀመመ አደንዛዥ ዕጽ ይዛ እንደነበር ያመነችው ብሪትኒ ግራይነር ትናንት ሞስኮ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርባ ቃሏን ሰጥታለች።

በአውሮፕላን ጣቢያው በቁጥጥር ስር ባዋሏት ወቅት አስተርጓሚው የሚተረጉምላት አሳሪዎቿ ይናገሩት ከነበረው እጅግ ጥቂቱን ብቻ እንደነበር እና ያሰሯት ባለሥልጣናት ምን እንደሚል ያላወቀችውን ሰነድ እንዳስፈረሟት ለፍርድ ቤቱ ቃሏን ሰጥታለች። ሱስ አስመጪ ቁስ የማጓጓዝ ወንጀል ፈጽማለች ከተባለች የአስር ዓመት እስራት ሊያስፈርድባት ይችላል።

XS
SM
MD
LG