ሃሺሽ አስገብተሃል በሚል በሩሲያ ላለፉት ሦስት ዓመታት ተኩል በእስር ላይ የነበረው አሜሪካዊ አስተማሪ በእስረኛ ልውውጥ ተለቋል።
መምህር ማርክ ፎግልን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በዋይት ሃውስ ተቀብለው አነጋግረውታል።
ማርክ ፎግል ወደ ሩሲያ ያስገባው ሃሺሽ በሐኪሙ የታዘዘለት እንደሆነ ታውቋል።
“በምድር ላይ ዕድለኛው ሰው እኔ እንደሆንኩ ይሰማኛል” ብሏል ፎግል።
ዶናልድ ትረምፕ ሩሲያ ፎግልን በመልቀቋ ሲያመሰግኑ፣ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ደግሞ አሜሪካም በበኩሏ አንድ ሩሲያዊ እስረኛ እንደምትለቅና ማንነቱም ወደ ሃገሩ እንደገባ እንደሚገለጽ አስታውቀዋል።
ተጨማሪ የታገቱ ሰዎችን መለቀቅ በተመለከተ ዛሬ ረቡዕ እንደሚያስታወቁም ትረምፕ ጠቁመዋል።
መድረክ / ፎረም