በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአንዳንድ የአሜሪካ ክ/ግዛት እየጨመረ በመጣው ወንጀል አሜሪካውያን ሰግተዋል


ፎቶ ፋይል፦ ኒው ኦርሊንስ፣ ሉዊዚያና፣ የቦርቦን ጎዳና ገጽታ በኮሮናቫይረስ ወረርሽ ወቅት እኤአ መጋቢት ወር 2020
ፎቶ ፋይል፦ ኒው ኦርሊንስ፣ ሉዊዚያና፣ የቦርቦን ጎዳና ገጽታ በኮሮናቫይረስ ወረርሽ ወቅት እኤአ መጋቢት ወር 2020

ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከመጣ ወዲህ አሜሪካውያን በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች የወንጀል ድርጊቶች እየበዙ መምጣታቸው ያሳሰባቸው መሆኑ ገለጹ፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው በተለይ በደቡብ ዩናይትድ ስቴትስ እንደ ኒው ኦረሊንስ ሉዊዚያና በመሳሰሉት ክፍለ ግዛቶች የሚገኙ ነዋሪዎች የወንጀል ድርጊቶቹ አሁንም እንደቀጠሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እኤአ በ2020 ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ከቀደመው የእኤአ 2019 ጋር ሲነጻጸር በ30 ከመቶ ማደጉ ተመልክቷል፡፡

ኤፍቢአይ ወንጀሎችን መዝግቦ መያዝ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ይህ የመጀመሪያው ትልቁ እድገት መሆኑን አስታውቋል፡፡

በተለይ እንደ ኒው ኦርሊንስ ባሉት ውስጥ የቤት ውስጥ ግድያዎችና የመኪና ስርቆት ከአገሪቱ አማካይ ቁጥር በላይ መጨመራቸው ተመልክቷል፡፡

እንደ ምሳሌነት ከተጠቀሱት በኒው ኦርለንስ እንደ እኤአ 2021 የተመዘገበው የቤት ውስጥ ግድያ መጠን ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ80 ከመቶ እድገቱ ሲያሳይ የተኩስ መጠንም በእጥፍ ማደጉ ተገልጿል፡፡ በዚህ በተያዘው የ2022 ዓመት የመኪና ስርቆት በ160 ከመቶ መጨመሩ ተመዝግቧል፡፡

ማሪያና ሮድርጊስ የተባሉት የኒው ኦርለንስ ነዋሪ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ እኤአ ከተማዪቱ ተዛውረው የመጡ መሆኑን ገልጸው “እዚሁ ስለኔ ጎበረቤትና አካባቢ በየቀኑ የማነበውና የምሰማው የወንጀል ዜና ቢያስደነግጠኝም ኑሮውዬን ከመቀጠል ሌላ አማራጭ የሌለኝ መሆኑን ገብቶኛል” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG