በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ እንደ ትረምፕ ዘመን ስደተኞችን ወደ ሜክሲኮ ድንበር ከተማ መመለስ ጀመረች


ፎቶ ፋይል፡-ከወላጆቹ ጋር ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሜክሲኮ የተመለሰው ታዳጊ በሲዳድ ጁሬዝ፣ ሜክሲኮ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ።
ፎቶ ፋይል፡-ከወላጆቹ ጋር ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሜክሲኮ የተመለሰው ታዳጊ በሲዳድ ጁሬዝ፣ ሜክሲኮ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ።

ዩናይትድ ስቴትስ ከትናንት ረቡዕ ጀምራ ስደተኞችን ሜክስኮ ውስጥ ወደ ምትገኘው ቱጃና የድንበር ከተማ መመለስ መጀመሯ ተገለጸ፡፡

ይህ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ዘመን፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች የፍርድ ቤት ሂደታቸውን ከዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ሆነው እንዲከታተሉ የሚያዘውን አሰራር ተመልሶ የሚከተል ነው ሲሉ የሜክሲኮ እና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት አስታውቀዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስና ሜክሲኮ ባለፈው ወር የፌደራል ፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባከበረ መልኩ አወዛጋቢ የሆነውን የስደተኞችን ደህንነት ጥበቃ ፕሮኮቶክል እንደገና ለመጀመር መስማማታቸው ይታወቃል፡፡

ዴሞክራቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከሳቸው በፊት በነበሩት የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የወጡትን ብዙዎቹን የከረሩ የስደተኞች ፖሊሲዎችን ለቀመልበስ እየታገሉ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG