በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሪፐብሊካን ፕሬዝደንታዊ እጩዎች የመጨረሻ ክርክር አደረጉ


የሪፐብሊካን ፕሬዝደንታዊ እጩዎች የመጨረሻ ክርክር
የሪፐብሊካን ፕሬዝደንታዊ እጩዎች የመጨረሻ ክርክር

በአሜሪካ የፕሬዝደንታዊ የምርጫ ፉክክር፣ አራት የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩዎች፣ አራተኛውን እና የመጨረሻውን ክርክር ትናንት ምሽት ሲያደርጉ፣ አንዳቸው ሌላው ላይ ሲጮሁ እና አንዱ ሌላው ላይ ትችት ሲሰነዝር አምሽተዋል።

እንዳለፉት ሶስት ክርክሮች ሁሉ፣ ትረምፖ በትናንቱ ምሽት ላይም አልተገኙም። ያም ሆኖ የቀድሞው የኒው ጀርሲ አገረ ገዥ ክሪስ ክሪስቲ፣ በትረምፕ ላይ ትችታቸውን ከመሰንዘር አላቆማቸውም። ሌሎቹን ተፎካካሪዎችም “ትረምፕን ለመውቀስ ትፈራላችሁ” ሲሉ ተደምጠዋል።

ትረምፕን ለመውቀስ ትፈራላችሁ”

ወደ 91 በሚሆኑ ክሶች ምክንያት ፍርድ ቤት በመመላለስ ላይ ያሉት ትረምፕ፣ ያም ሆኖ ፉክክሩን እየመሩ እንደሆነ የሕዝብ ድምፅ መለኪያ ጥናቶች ያሳያሉ።

ባለፈው ሳምንት የተካሄደ የሕዝብ ድምፅ መለኪያ እንዳመለከተው፣ ትረምፕ 68 በመቶ በማግኘት፣ ከፍሎሪዳው አገረ ገዥ ራን ደሳንቲስ እና በተመድ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ከነበሩት ኒኪ ሄሊ ቀድመው ይገኛሉ።

የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነትን በተመለከተ፤ እጩዎቹ፣ እስራኤል ካለ አሜሪካ ጥልቃ ገብነት ጦርነቱን ማካሄድ ሊፈቀድላት ይገባል ብለዋል።

የፍሎሪዳው አገረ ገዥ ራን ደሳንቲስ፤ “የባይደን አስተዳደር እስራኤል ራሷን መከላከል እንዳትችል እጇን ሊያስር እየሞከረ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG