በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በትዊተር ጉዳይ ናይጄሪያን አወገዘች


ናይጄሪያ የማህበራዊ መገናኛ ትዊተርን አገልግሎት በመዝጋት የወሰደችውን እርምጃ ዩናይትድ ስቴትስ በድጋሚ አውግዛዋለች። ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴተስ ባለሥልጣናት የናይጄሪያ መንግሥት አድራጎት የፖለቲካ ምህዳሩን የማጥበብ ምልክት ነው ብለውታል።

ትዊተር በቅርቡ የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ሙሃማዱ ቡሃሪ በማህበራዊ መገናኛ ገፃቸው /ትዊተር/ ላይ ያሰፈሩትን ጽሁፍ ከሰረዘባቸው በኋላ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ላልተወሰነ ጊዜ ማገዳቸው አይዘነጋም።

ከትውልደ ናይጄሪያውያን የሚወለዱት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ረዳት ሚኒስትር አኩና ኩክ ትናንት በአትላንቲክ ካውንሲል የውይይት መድረክ ላይ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸው ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ ጉዳዮች ገንቢ ሚና መጫወት የምትችል ሃገር ሆና ሳለ የፖለቲካው ምህዳር እየጠበበ የመሄዱ እና የመናገር ነጻነት መታፈኑን የሚያሳዩት ምልክቶች አሳሳቢ ናቸው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG