በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ተዋጊ ጀቶችና የዩናይትድ ስቴትስ ድሮን ግጭት ቪዲዮ ተለቀቀ


የሩሲያ ተዋጊ ጀቶችና የዩናይትድ ስቴትስ ድሮን ግጭት ቪዲዮ ተለቀቀ
የሩሲያ ተዋጊ ጀቶችና የዩናይትድ ስቴትስ ድሮን ግጭት ቪዲዮ ተለቀቀ

የዩናይት ስቴትስ ጦር፣ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ በጥቁር ባህር ላይ በሩሲያ ጦር ተሰናክሎ የወደቀውን የዩናይትድ ስቴትስ ሰው አልባ የቅኝት አውሮፕላን (ድሮን) የሚያሳይ ቪዲዮ ዛሬ ሀሙስ ይፋ አድርጓል፡፡

የቪዲዮው ምስል የሩሲያ ሱኮይ ሱ 27 ተዋጊ ጀት MQ-9 የተባለውን የዩናይትድ ስቴትስ ድሮን ተጠግቶ ሲከተል ከቆየ በኋላ ከላይ አልፎ በመሄድ ነዳጅ ሲረጭ አሳይቷል፡፡

ሁለተኛው ሱኮይ ኤስ 27 ተዋጊ ጀትም በተመሳሳይ ወደ ድሮኑ ከተጠጋ በኋላ የቪዲዮ ምስል የተቋረጠ ሲሆን ይህም የሆነው ተዋጊ ጀቱ ከድሮኑ ጋር በመላተሙ ነው ሲል የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አስታውቋል፡፡

መጨረሻው ላይ ከተወሰደው የቪዲዮ ምስል መረዳት እንደተቻለው ተዋጊ ጀቱ እጥፋት ከደረሰበት ከድሮኑ ተርገብጋቢ አካል ጋር ሲጋጭ ያሳያል፡፡

የቪዲዮው ምስል የተለቀቀው የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተር ከሩሲያው አቻቸው ጋር ስለክስተቱ በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG