በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ አስተዳደር "ከፍተኛ አደጋ የሚደቅኑ" ተብለው የተፈረጁ ሀገሮች

የትረምፕ አስተዳደር "ከፍተኛ አደጋ የሚደቅኑ" ተብለው ከተፈረጁ አስራ አንድ ሃገሮች ወደዩናይትድ ስቴትስ ለመምጣት አመልካቾችን ታሪክ ላይ ጥልቅ የሆነ ፍተሻ በማድረግ የስደተኛ መቀበል ፖሊሲውን እያጠበቀ መሆኑ ተገልጿል።

የትረምፕ አስተዳደር "ከፍተኛ አደጋ የሚደቅኑ" ተብለው ከተፈረጁ አስራ አንድ ሃገሮች ወደዩናይትድ ስቴትስ ለመምጣት አመልካቾችን ታሪክ ላይ ጥልቅ የሆነ ፍተሻ በማድረግ የስደተኛ መቀበል ፖሊሲውን እያጠበቀ መሆኑ ተገልጿል።
ባለሥልጣናት ይህንኑ ትናንት ይፋ ባደረጉበት ወቅት የትኞቹ ሃገሮች አንደሆኑ ለጋዜጠኞች በዝርዝር ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ይሁን እንጂ ሀገሮቹ ግብጽ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን እና የመን እንደሆኑ በስፋት ሲዘገብ ቆይቱዋል።
አንዱ ከፊተኛው የሚለየው ከአስራ አንዱ ሀገሮች በሆኑት ስደተኞች ላይ ይበልጡን ጥልቀት ያለው ቃለ መጠይቅ የሚደረግ መሆኑ ነው ብለዋል። አብዛኛው የስደተኞች አቀባበል ለውጥ እኤአ ከፊታችን መጋቢት ወር መጨረሻ ሥራ ላይ እንደሚውል ከባለሥልጣናቱ አንዱ ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG