በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃውሞ ሰልፎች በዓለም ዙሪያ


APTOPIX Minneapolis Police Death Washington Protest
APTOPIX Minneapolis Police Death Washington Protest

ኒውዚላንድ ውስጥ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ አፍሪካዊ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስች እጅ መሞቱን በመቃወም፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ በመደገፍ ዛሬ ሰልፍ አካሄደዋል።

ኦክላንድ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፈኞቹ፣ ወደ የአሜሪካ ቆንስላ ሄደው፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚሰሙትን፣ “የጥቁሮች ህይወትም ዋጋ አለው” እና “ፍትህ ሳይኖር ሰላም አይኖርም” የሚሉትን መፈክሮች እንዳስተጋቡ ተዘግቧል።

ትናንት ደግሞ በብሪታንያ፣ በብራዚል፣ በካንዳና በሌሎችም ሀገሮች ሰልፎች ተካሄደዋል፤ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ በማዕካላዊው ለንደን ተሰባሰበው፣ አሜሪካ ውስጥ የጆርጀ ፍሎይድ በፖሊሶች እጅ መሞትን በማውገዝ ተቃውሞ ያሰሙትን በመደገፍ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።

ፍሎይድ ባለፈው ሳምንት በሚኒሶታ ክፍለ-ግዛት ሚንያፖሊስ ከተማ፣ አንድ ነጭ ፖሊስ፣ ጉልበቱን አንገቱ ላይ ተጭኖ ከስምንት ደቂቃዎች በላይ በመቆየቱ ለህልፈት ተዳርጓል። ይህ የሆነውም መሬት ላይ ዘርግተውት፣ እጁ በካቴና ታስሮ “መተንፈስ አልቻልኩም” እያለ ድምጹን እያሰማ በነበረበት ወቅት ነው።

ዴንማርክ ላይ ትናንት የተቃውሞ ሰልፈኞች፣ ኮፐንሀገን ወደ ሚገኘው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሄደው “ጥቁሮችን መግደል ይቁም” የሚሉ መፈክሮችን አንገበው አስተጋብተዋል። ጀርመን ላይ ደግሞ “ፖሊሶችን ተጠያቂ አድርጉ”፣ “ፖሊሶች ራሳቸው ገዳይ ሲሆኑ ማንን መጥራት ይቻላል?" የሚሉ መሪ ቃሎችን አንነግበው ታይተዋል።

XS
SM
MD
LG