በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በፖሊሶች አሰራር ለውጥ የማድረግ እርምጃ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል


የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ፣ በአንዳንድ የፖሊሶች አሰራር ላይ፣ ለውጥ የማድረግ እርምጃ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዓላማው የፖሊሶችን አሰራር ለማስተካከል መሆኑን፣ አንድ ከፍተኛ የአስተዳስደሩ ባለሥልጣን ገልጸዋል።

አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ፖሊሶች በኃይል አጠቃቀም ላይ ያላቸውን አያይዝ ለማስተካክል ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።

ሌላው ዘዴ ደግሞ፣ ፖሊሶች ጥቃት አልባ የሆነ የድረሱልን የስልክ ጥሪ ሲደረግላቸው፣ ከማኅበራዊ ኑሮ ሰራተኞች ጋር ሆነው የሚሄዱበት አገልግሎት መመስረት እንደሆነ ተገልጿል። በተለይም ከአዕምሮ ህመመና ከአደንዛዥ ዕፅ መውሰድ ጋር የተያያዘ ሲሆን ነው ተብሏል።

በሀገሪቱ ዙርያ የፖሊሶች አያያዝን በሚመለከት፣ ስፊ ለውጥ እንዲደረግ፣ በሀገሪቱ ምክር ቤት ውይይት እተካሄደ መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG