በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህዝባዊ ሰልፍ በአሜሪካ ከተሞች እንደቀጠለ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የተቃውሞ ሰልፈኞች ከዋይት ኃውስ ቤተ-መንግሥት ፊት ለፊት - ዋሺንግተን ዲሲ
ፎቶ ፋይል፦ የተቃውሞ ሰልፈኞች ከዋይት ኃውስ ቤተ-መንግሥት ፊት ለፊት - ዋሺንግተን ዲሲ

አፍሪካዊ አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በሚኒያፖሊስ ሚኔሶታ በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ በመገደሉ በአሜሪካ ከተሞች ሲካሄድ የቆየው የተቃውሞ ሰልፍ የቀጠለ ሲሆን፣ የትናንት ማታ በአብዛኛው ሰላማዊ እንደነበርና ብዙም የግጭት ተግባር እንዳልነበረ ተዘግቧል።

ኒውዮርክንና ዋሺንግተንን ባቀፉ የሀገሪቱ ክፍሎች የተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች፣ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት የሚጀምረውን የሰዓት እላፊ ገደብን ጥሰው ያመሹ ቢሆንም፣ ከበፊቶቹ ሰልፎች በተለየ ረጋ ያሉ እንደነበሩ ታውቋል።

የዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሞዩሪየል ባውዘር፣ በከተማይቱ የተደነገገው የሰዓት እላፊ ገደብ፣ እየተነሳ መሆኑን ገልጸዋል። በቋሚነት ይሁን በጊዚያው መልክ ግን ግልጽ አላደረጉም።

ከተለያዪ የፊደራል አገልግሎቶች የተውጣጡ ወታደራዊ ፖሊስና የህግ አስከባሪ ኃይሎች፣ በዋሺንግተን ዲሲ ተመድበው ነበር። የነሱ በዋሺንግተን መመደብም፣ በከተማይቱ ባለሥጣኖችና በፌዴራሉ መንግሥት መካከል ቅራኔ ፈጥሯል።

የዋሺንግተን ዲሲ ባለሥልጣኖች ለተቃውሞ ሰልፉ ምላሽ ሲባል የተመደቡት የፌዴራል መንግሥት ኃይሎች፣ ከዋይት ኃውስ አካባቢ ርቀው ሊሄዱ አይችሉም በማለት ተከራክረዋል። በዋሺንግተን ዲሲ ነገ ትልቅ የተውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG