በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

በዩናይትድ ስቴትስ ትናንት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ አሸናፊው ማን እንደሆነ ገና አልታወቀም። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ብዙ ስዎች፣ በፖስታ ቤት በኩል የመርጡባቸው ክፍላተ-ግዛት፣ የምርጫ ውጤት ገና እየተቆጠረ በመሆኑ ውጤቱ ዘግይቷል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና ዲሞክራቱ ተወዳዳርያችው ጆ ባይደን፤ በየበኩላቸው እንደሚያሸንፉ በተጠበቁባቸው ክፍላተ-ግዛት አሸንፈዋል።

በሃገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙት ሰሜን ካሮላይና፣ ጆርጂያና ፔንሲልቬንያ ክፍላተ ግዛት፣ በመካከለኛው ምዕራብ ሚችገንና ዊስካንሰን፣ በደቡብ ምዕራብ ደግሞ አሪዞና፣ ትላንትና በቅድመ-ምርጫ ቀን የተሰጡ፣ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ድምጾችን፣ ባለሥልጣኖች እየቆጠሩ ነው።

ትረምፕ ታድያ ዛሬ ማለዳ ላይ፣ ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ሆነው ሲናገሩ፣ በምርጫው አሸንፊያለሁ ብለው እንደሚያምኑ ገልጽው፣ የድምጽ ቆጠራው እንዲቆም፣ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እሄዳለሁ ብለዋል።

የባይደን የምርጫ ዘመቻ ክፍል በበኩሉ፣ ፕሬዚዳንቱ የምርጫ ቆጠራውን ለማቆም መዛታቸው፣ አስደንጋጭ ነው ካለ በኋላ፣ ከምርጫው ቀን በፊት ለመምረጥ የወሰኑትን አሜሪካውያን ዲሞክራስያዊ መብቶችን፣ የሚረግጥ ነው ሲል ነቅፏል።

XS
SM
MD
LG