ዋሽንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ዓርብ ኦክላሆማ ተልሳ ከተማ ላይ ለሚያደርጉት ህዝባዊ ስብሰባ ለመታደም በብዙ አስር ሺዎች እየተሰባሰቡ ነው
ፕሬዚደንቱ ብዛት ያለው ደጋፊ የሚገኝበት ንግግር ሲያደርጉ በኮቪድ አስራ ዘጠኝ ምክንያት የተለያዩ የእንቅስቃሴ ክልከላዎች ከታዘዙና በሃገሪቱ ዙሪያ የፖሊስ የጭካኔ አድራጎቶችን ከሚቃወሙት ሰልፎች ወዲህ ይህ የዛሬው የመጀመሪያ ነው
በጉባዔው ላይ የሚሳተፉ ሁሉ ፊታቸውን በጭንብል እንዲሸፈኑ ለማስገደድ ከነዋሪዎች የቀረበውን ጥያቄ የክፍለ ግዛትዋ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል
የፕሬዚደንቱ የምርጫ ዘመቻ እንዳስታወቀው የስብሰባው አደራጆች ለሚፈልጉ ተሳታፊዎች ጭንብልና የእጅ ማጽጃ ይሰጣሉ፤ የተሳታፊዎች የሰውነት ሙቀትም ይለካል
ብዛት ያለው ሰው የሚታደምባቸው ስብሰባዎች ለኮሮና ቫይረስ መተላለፍ አመቺ እንደሆኑ የጤና ባለስልጣናት ያስጠነቅቃሉ