በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ኮንግረስ የተወረረበት አንደኛ ዓመት እየታሰበ ነው


Prezidan Joe Biden pale ak pep Ameriken an depi Statuary Hall nan Capitol la nan Washington, premye anivese atak 6 Janvye a.
Prezidan Joe Biden pale ak pep Ameriken an depi Statuary Hall nan Capitol la nan Washington, premye anivese atak 6 Janvye a.

በኮንግረሱ ላይ በተካሄደው ወረራና ጥቃት ውስጥ ተሣትፈዋል የተባሉ 725 ሰዎች ተይዘው ታስረዋል።

በዕለቱ ስለተከሰተው ሁኔታና ስለ አድራጎቶቻቸው በተለያዩ ወንጀሎች ተከስሰው የተፈረደባቸው ሰዎች ከአንድ ዓመት በኋላ እየተናገሩ ናቸው።

ፕሬዘዳንት ጆ ባይደንና ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ በምክር ቤቱ ላይ የተፈፀመው ጥቃት በእንደራሴዎች፣ በአሜሪካ ዴሞክራሲና በሕገመንግሥቱ ላይ ያሳደረውን ጫና የዳሰሱ ንግግሮች አድርገዋል።

“በሕገ መንግሥታችን ላይ ትልቅ ሥጋት ተጋርጦበታል” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ ደግሞ “የምርጫ ውጤትን ለመቀልበስ እስከመሞከር ያደረሰን ሁኔታ የሚያሳየው ዴሞክራሲ እጅግ ስስና ተሰባሪ መሆኑን ነው፤ ካልተንከባከብነውና ካልጠበቅነው ይወድቃል” ሲሉ አሳስበዋል።

ሙሉውን ዘገባ ከተጠናቀረው የድምጽ ፋይል ያገኛሉ።

የአሜሪካ ኮንግረስ የተወረረበት አንደኛ ዓመት እየታሰበ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:09 0:00


XS
SM
MD
LG