በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጉዞ ዕገዳ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያዘዙት የጉዞ ዕገዳ በተመለከተ በበታች ፍርድ ቤቶች ሙግቱ እንደቀጠለ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዕገዳው እንደፀና እንዲቆይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትናንት ውሳኔ ሰጠ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያዘዙት የጉዞ ዕገዳ በተመለከተ በበታች ፍርድ ቤቶች ሙግቱ እንደቀጠለ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዕገዳው እንደፀና እንዲቆይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትናንት ውሳኔ ሰጠ።

ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች ሰባቱ አስተዳደሩን ደግፈው ውሳኔ ሲሰጡ ሁለቱ ዳኛ ሩት ባደር ጊንስበርግ እና ዳኛ ሶኒያ ሶቶማየር ዕገዳው በከፊል እንደታገደ እንዲቆይ ብለዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔው ላይ የደረሰበትን ምክንያት አልገለፀም።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለሦስተኛ ጊዜ ያወጡት የጉዞ ዕገዳ አብዛኛው ሕዝባቸው ሙስሊም ከሆኑ ሥምንት ሃገሮች የሆኑ አብዛኞች መንገደኞች እንዳይገቡ ይከለክላል። ሀገሮቹ ቻድ፣ ሊቢያ፣ ኢራን፣ ሶማሊያ፣ ሶሪያ፣ ቬንዙዌላ፣ የመንና ሰሜን ኮሪያ ናቸው።

ይህን የፕሬዚዳንቱን ዕገዳ የሜሪላንድና የሃዋይ ክፍለ ሀገሮች የበታች ፍርድ ቤቶች ዳኞች ሥራ ላይ እንዳይውል አግደውታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG