በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዩናይትድ ስቴትስ


ትናንት በዩናይትድ ስቴትስ በኮቪድ-19 የታመሙ 61,964 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸው ታወቀ። ይህ አሃዝ ባለፈው ሚያዚያ አጋማሽ ላይ የነበረውን አሃዝ ከሁለት ሺህ በላይ የሚበልጥ መሆኑም ተገልጿል።

ሆስፒታል የሚገቡት ህሙማን ቁጥር መጨመሩ በተለይም በማዕከላዊ ምዕራብ በርካታ ክፍለ ግዛቶች ያሉ የጤና ተቋማት አቅም ላይ ብርቱ ጫና እያሳደረ መሆኑ ተመልክቷል። አንዳንዳቹ ሆስፒታሎች የመኪና ማቆሚያቸው ላይ የህሙማን ማሳረፊያ ድንኳኖች እንዲተክሉ ወይም ወደሌሎች ሆስፒታሎች እንዲልኩ ተገደዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትናንት ብቻ 130, 989 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ሃገሪቱ በጠቅላላው 10 ነጥብ አንድ ሚሊዮን የቫይረሱ ተጋላጮች ይዛ በዓለም ቀዳሚው ስፍራ ላይ ነች።

በሃገሪቱ በዚህ የፈረንጆች ህዳር ወር የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ብቻ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የኮሮና ተግላጮች መገኘታቸው ታውቋል።

XS
SM
MD
LG