በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክ ፖምፒዮ አርጀንቲና መጓዛቸው ተገለፀ


የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ
የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ

የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ አርጀንቲና ይገኛሉ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በሽብርተኛነት ላይ ለምታካሂደው ትግል የላትን የአማሪካ መሪዎች ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ቅስቀሳ ለማድረግ ነው።

ከፍተኛው የአሜሪካ ዲፕሎማት ዛሬ ዐርብ ቦነስ አይሬስ ላይ ንግግር እንደሚያደርጉም ተገልጧል።

ባለፈው ሰኞ የአርጀንቲና የደኅንነት ባለሥልጣናት፣ ሊባኖስ ውስጥ የሚገኘውን የሕዝብ አላህ አማፂ ቡድን፣ በሽብርተኛነት መፈረጃቸው ይታወቃል። ይህም ሽብርተኛነትን በመዋጋት ረገድ ዩናይትድ ስቴትስ በዓለማቀፍ ደረጃ የሚኖሯትን ሸሪክ ሀገሮች ቁጥር እንደሚጨምርላት ነው የተነገረው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG