በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክ ፓምፔዮ በበርሊን


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ

የበርሊን ግንብ ከፈረሰ ሦስት አስርተ-ዓመታት ቢያልፉም ዋሽንግተንና አጋሮችዋ ሀገሮች አሁንም ኮሙኒስት ተቃዋሚዎቻቸውን መገዳደራቸው አልቀረም። ነጻው ዓለም ደግሞ ከሩስያና ከቻይና የሚደቀኑበትን አደጋዎች መከላከሉን መቀጠል አለበት ትላለች ዩናይትድ ስቴትስ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ በርሊን ባለው የብራንደንበርግ በር ሆነው ዛሬ ባደረጉት ንግግር “ሩስያ ጎረቤቶችዋ ሀገሮችን ትወራለች። የፖለቲካ ተቃዋሚዎችዋን ትግድላለች ብለዋል። የሩስያ ባለሥልጣኖች በክሪሚያ ታርታሮችና የሩስያን ወረራ በመቃወም በሚሰሩ ኡክራይናውያን ላይ “ወረራ ያካሄዳሉ፣ ሰቆቃም ይፈጽማሉ” ሲሉም ፓምፔዮ ከሰዋል።

ከፍተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት ቻይናንም ነቅፈዋል።

“ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ በሀገሪቱ ላይ አዲስ የአምባገነንነት ራዕይ እየቀየሰ ነው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ህዝቡን የመጨቆን ዘዴ ይጠቀማል። የሚነቅፉትን ሰዎች የመንቀሳቀስ መብት ያግዳል፣ ከሺንዢያንግ ወደ ውጭ ሃገራት የተሰደዱት ሙስሊም ቻይናውያን ቤተሰቦቻን ያዋክባሉ” ብለዋል ፓምፔዮ።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጌንግ ሽዋንግ በበኩላቸው ፓምፔዮ ቀደም ሲል ስለቻይና ኮሙኑስት ፓርቲ ለተናገሩት ምላሽ ሰጥተዋል። “ ቻይና የምትደቅነው አደጋ አለ በማለት ፓምፔዮ የቻይና የፖለቲካ ስርዓትን ነቅፈዋል።

አነጋገራቸው በርእዮተ ዓለም ላይ ባላቸው ያለመቻቻል አመለካከትና በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት አስተሳሰብ የተሞላ ነው። የቻይና መንግሥት አብክሮ ይቃወመዋል ሲሉ ቃል አቀባዩ ምላሽ ሰጥተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG