በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ክሪስ ክሪስቲ የምርጫ ዘመቻቸውን አቋርጠው ወጡ


የቀድሞው የኒው ጀርሲ አገረ ገዥ ክሪስ ክሪስቲ የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ
የቀድሞው የኒው ጀርሲ አገረ ገዥ ክሪስ ክሪስቲ የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ

የቀድሞው የኒው ጀርሲ አገረ ገዥ ክሪስ ክሪስቲ የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ ሆኖ ለመቅረብ የያዙትን ዘመቻ አቋርጠው ወጡ። ክርስቲ የወሰዱት እርምጃ በአንድ በኩል ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው እጩ ሆኖ ለመቅረብ የያዙትን ግስጋሴ ለመግታት የተደረገ ጥረት ተደርጎም ታይቷል።


ክሪስቲ ይህን ውሳኔያቸውን ይፋ ያደረጉት ትናንት ረቡዕ ማምሻው ላይ በ2024ቱ የምርጫ ሂደት አምስተኛው የሪፐብሊካን ተፎካካሪዎች እርሳቸው የሌሉበት ክርክር ከመጀመሩ ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ በኒው ሃምፕሸር ክፍለ ግዛት ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት ሥነ ስርዓት ነው።


የትራምፕ ተቺዎች ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ሌላ ፓርቲውን የሚወክል ዕጩ አሸንፎ እንዲወጣ እና ፓርቲያቸውን አንድ ለማድረግ በያዙት ጥረት ክርስቲ የምርጫ ዘመቻቸውን አቋርጠው ከፉክክሩ ይወጡ ዘንድ ብርቱ ጫና ሲያደርጉባቸው ነበር።
ይሁንና ክሪስቲ ፈጥነው ከቀድሞ ተፎካካሪዎቻቸው ለአንዳቸው ድጋፋቸውን ይሰጡ እንደሁ ግን እስካሁን ግልጽ ባይሆንም፤ የምርጫ ዘንመቻቸውን ማብቃት ይፋ ያደረጉበትን ንግግራቸውን ከማሰማታቸው አስቀድሞ “ኒኪ ሄሊ እንዳይሆኑ ሆነው ይሸነፋሉ" ሲሉ በቀጥታ ማይክራፎን ተሰምቶ ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG